+ -

عَنْ ‌أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ: أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«صَلَاةٌ فِي مَسْجِدِي هَذَا خَيْرٌ مِنْ أَلْفِ صَلَاةٍ فِيمَا سِوَاهُ إِلَّا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1190]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1190]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በርሳቸው መስጂድ የሚሰገድ ሶላትን ደረጃ ገለፁ። እርሱም መካ ውስጥ ከሚገኘው ከተከበረው መስጂድ ውጪ ምድር ላይ በሚገኙ መስጂዶች ከሚሰገድ ሶላት ሁሉ በአንድ ሺህ እጥፍ ይበልጣል። በተከበረው መስጂድ (መስጂደል ሐራም) የሚሰገድ ሶላት ግን በርሳቸው መስጂድ ከሚሰገድ ሶላትም ይበልጣል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በተከበረው መስጂድና በነቢዩ መስጂድ የሚሰገድ ሶላት ምንዳ እጥፍ ድርብ መሆኑን እንረዳለን።
  2. በተከበረው መስጊድ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ በሚገኙ መስጂዶች ከሚሰገዱ ሶላቶች በመቶ ሺህ በላጭ ነው።