عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤمنين رضي الله عنها:
أَنَّ أُمَّ سَلَمَةَ ذَكَرَتْ لِرَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَنِيسَةً رَأَتْهَا بِأَرْضِ الْحَبَشَةِ، يُقَالُ لَهَا مَارِيَةُ، فَذَكَرَتْ لَهُ مَا رَأَتْ فِيهَا مِنَ الصُّوَرِ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أُولَئِكَ قَوْمٌ إِذَا مَاتَ فِيهِمُ الْعَبْدُ الصَّالِحُ، أَوِ الرَّجُلُ الصَّالِحُ، بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، أُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 434]
المزيــد ...
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦
ኡሙ ሰላማ ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሀበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላየቻቸው ምስሎች ነገረቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡ፤ በውስጡም (ምስሉን) ስእላ ስእል የሚቀርፁ ናቸው። እነዚህ ህዝቦች አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ (መጥፎ) ፍጡራን ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 434]
የአማኞች እናት ኡሙ ሰለማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - በሐበሻ ምድር ማሪያህ የምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስእሎች፣ ጌጦችና ቅርፆች ማየቷን በመደነቅ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የነዚህን ስእሎች መደረግ ምክንያት ገለፁ። "እነዚህ አሁን አንቺ የምታወሺያቸው በመካከላቸው ደግ ሰው የሞተ ጊዜ በቀብሩ ላይ መስጂድ ይገነቡና በውስጡ ይሰግዱበታልም እነዚህንም ስእሎች ይስላሉ።" አሉ። ይህንን የሚፈጽም ሰው አላህ ዘንድ ክፉ ፍጡር እንደሆነ ገለፁ፤ ምክንያቱም ይህ ድርጊቱ በአላህ ወደ ማጋራት ስለሚያዳርስ ነው።