عن حُذَيْفَةَ رضي الله عنه:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَقُولُ بَيْنَ السَّجْدَتَيْنِ: «رَبِّ اغْفِرْ لِي، رَبِّ اغْفِرْ لِي».
[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه وأحمد] - [سنن ابن ماجه: 897]
المزيــد ...
ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል 'ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ' 'ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!' ይሉ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 897]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል በሚቀመጡ ጊዜ "ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ" "ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!" ይሉ ነበር። ይደጋግሟትም ነበር።
"ረቢጝፊርሊ" ማለት አንድ ባሪያ ከጌታው ወንጀሎቹን እንዲምረውና ነውሮቹን እንዲሸሽግለት መፈለጉ ነው።