عَن ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما:
أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَرْفَعُ يَدَيْهِ حَذْوَ مَنْكِبَيْهِ إِذَا افْتَتَحَ الصَّلَاةَ، وَإِذَا كَبَّرَ لِلرُّكُوعِ، وَإِذَا رَفَعَ رَأْسَهُ مِنَ الرُّكُوعِ، رَفَعَهُمَا كَذَلِكَ أَيْضًا، وَقَالَ: «سَمِعَ اللَّهُ لِمَنْ حَمِدَهُ، رَبَّنَا وَلَكَ الحَمْدُ»، وَكَانَ لاَ يَفْعَلُ ذَلِكَ فِي السُّجُودِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 735]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና ለሩኩዕ ተክቢራ በሚያደርጉ ጊዜ እጃቸውን በትከሻቸው ትይዩ ከፍ ያደርጉ ነበር። ልክ እንደዚሁ ከሩኩዕ ራሳቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜም እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር። "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ፣ ረበና ወለከል ሐምድ" ይሉም ነበር። ሱጁድ ላይ ግን ይህንን አያደርጉም ነበር።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 735]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ በሶስት ስፍራዎች በትከሻቸው ትይዩ እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር።
የመጀመሪያው ወቅት: የመክፈቻ ተክቢራ ወቅት ሶላትን የጀመሩ ጊዜ ነው።
ሁለተኛው: ለሩኩዕ ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ነው።
ሶስተኛው: ጭንቅላታቸውን ከሩኩዕ ቀና ያደረጉና "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ ረበና ወለከል ሐምድ" ያሉ ጊዜ ነው።
ሱጁድ ማድረግ በሚጀምሩበት ወቅትም ሆነ ከሱጁድ በሚነሱበት ወቅት ግን እጃቸውን ከፍ አያደርጉም ነበር።