عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، إِذَا كَبَّرَ فِي الصَّلَاةِ، سَكَتَ هُنَيَّةً قَبْلَ أَنْ يَقْرَأَ، فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ بِأَبِي أَنْتَ وَأُمِّي أَرَأَيْتَ سُكُوتَكَ بَيْنَ التَّكْبِيرِ وَالْقِرَاءَةِ، مَا تَقُولُ؟ قَالَ «أَقُولُ: اللهُمَّ بَاعِدْ بَيْنِي وَبَيْنَ خَطَايَايَ كَمَا بَاعَدْتَ بَيْنَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ، اللهُمَّ نَقِّنِي مِنْ خَطَايَايَ كَمَا يُنَقَّى الثَّوْبُ الْأَبْيَضُ مِنَ الدَّنَسِ، اللهُمَّ اغْسِلْنِي مِنْ خَطَايَايَ بِالثَّلْجِ وَالْمَاءِ وَالْبَرَدِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 598]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። እኔም የአላህ መልክተኛ ሆይ! እናትና አባቴ ፊዳ ይሁንሎና በተክቢራ እና በፋቲሓ መካከል ዝምታዎን አይቻለሁና ምንድን ነው የሚሉት? አልኳቸው። እርሳቸውም " 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመጝሪብ አልላሁምመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዹ ሚነድደነስ፣ አልላሁምመ ኢጝሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ' ነው የምለው" አሉኝ። (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ መካከል እንዳራራቅከው በኔና በወንጀሌ መካከል አራርቅ! አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፉ እንደሚጠራው እኔንም ከወንጀሎቼ አጥራኝ! አላህ ሆይ በጤዛ፣ በውሃና በበረዶ ከወንጀሎቼ እጠበኝ። ማለት ነው።)»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 598]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ፋቲሓ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። በዚህ ዝም ባሉበት ወቅትም ሶላታቸውን በአንዳንድ ዱዓ ይከፍታሉ። ከነዚህ ከተላለፉልን ዱዓዎች መካከልም: "አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመጝሪብ አልላሁመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዱ ሚነደነስ፣ አልላሁመ ኢጝሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ።" ሰውዬው በዚህ ዱዓ በምስራቅና ምዕራብ መካከል ፈፅሞ መገናኘት እንደማይኖረው ሁሉ ከርሱ ጋር በማይገናኙ መልኩ በርሱና በወንጀሎቹ መካከልም አላህ ዐዘ ወጀል እንዲያራርቅ እና ወንጀል ላይ እንዳይወድቅ፤ ወንጀል ላይ ከወደቀ እንኳ ነጭ ልብስ ከእድፍ እንደሚጠራው ከወንጀሉ እንዲያጠራውና እንዲያስወግድለት፣ ከወንጀሉ እንዲያጥበውና የወንጀሉን ሀሩርና ወላፈንንም በውሃ፣ በጤዛና በረዶ እንዲያቀዘቅዝለት ነው ዱዓ የሚያደርገው።