عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما:
أَنَّ نَبِيَّ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَقُولُ عِنْدَ الْكَرْبِ: «لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ الْعَظِيمُ الْحَلِيمُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَرَبُّ الْأَرْضِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2730]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል ዐርሺል ከሪም" (ትርጉሙም፡ "ከታላቁና ቻይ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ፣ ከተከበረው ዐርሽ ጌታ አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" ማለት ነው።)
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2730]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ችግርና ጭንቀት በርሳቸው ላይ በሚበረታ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። "ታላቅ በሆነው" ክብሩ፣ በማንነቱ፣ በባህሪውና በድርጊቱ ነገሩ የላቀ፤ "ቻይ" ወንጀለኛን በመቅጣት የማይቸኩል ይልቁንም የሚያዘገይ፤ መቅጣት እየቻለ ይቅር የሚል፤ በሁሉም ነገር ላይም ቻይ የሆነ ነው። "ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የታላቁ ዐርሽ ፈጣሪ ነው። "የሰማያትና የምድር ጌታ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" የሰማያትና ምድር ፈጣሪ፤ በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረ፤ ባለቤቱ፣ አስተካካዩና እንደፈለገው የሚያስተናብረው ነው። "የተከበረው ዐርሽ ጌታ" የተከበረውን ዐርሽ የፈጠረ ነው።