+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَدْعُو بِدَعْوَةٍ لَيْسَ فِيهَا إِثْمٌ، وَلَا قَطِيعَةُ رَحِمٍ، إِلَّا أَعْطَاهُ اللهُ بِهَا إِحْدَى ثَلَاثٍ: إِمَّا أَنْ تُعَجَّلَ لَهُ دَعْوَتُهُ، وَإِمَّا أَنْ يَدَّخِرَهَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ، وَإِمَّا أَنْ يَصْرِفَ عَنْهُ مِنَ السُّوءِ مِثْلَهَا» قَالُوا: إِذنْ نُكْثِرُ، قَالَ: «اللهُ أَكْثَرُ».

[صحيح] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 11133]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
«ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።»

[ሶሒሕ ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 11133]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ወንጀልና በደል ለመፈፀም እንዲገራለት መለመንን የመሰለ ወንጀል ባልሆነ፤ በቅርብ ዘመዱና በልጆቹ ላይ እርግማን መለመንን የመሰለ ዝምድና መቁረጥ ባልሆነ ዱዓእ አላህን የለመነና የጠየቀ ጊዜ አላህ በዱዓው አማካይነት ከሶስት ነገሮች አንዱን ይሰጠዋል ብለው ተናገሩ፡ ወይ የለመነውን በፍጥነት ይሰጠዋል፤ ወይም የትንሳኤ ቀን ደረጃውን ከፍ እንዲያደርግለት ወይም እንዲታዘንለትና ወንጀሉን መማሪያ እንዲሆንለት አላህ ምንዳውን ያደልብለታል፤ ወይም የለመነውን የሚያክል የሆነ መጥፎን ነገር በዱንያው ውስጥ ይከላከልለታል። ሶሐቦችም ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ስለዚህ ከነዚህ ደረጃዎች አንዱን እንድናገኝ ዱዓን እናብዛ እንዴ?" አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አላህ ዘንድ ያለው እናንተ ከምትጠይቁትም በላይ ትልቅና ብዙ ነው። የርሱ ስጦታ አያልቅምም አይቀንስምም።" አሏቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሙስሊም ዱዓ የማትመለስ ተቀባይነት ያላት ናት። ነገር ግን ይህ መስፈርቶቿና ስነስርዓቷ የተሟላ ጊዜ ነው። ስለዚህም አንድ ባሪያ አብዝቶ ዱዓ ማድረግ እንጂ የዱዓውን ውጤት በፍጥነት ለማግኘት መቸኮል የለበትም።
  2. የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት የፈለግነውን በማግኘት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። በዱዓው አማካይነት ወንጀሉን ሊምረው ወይም መጪው ዓለም ላይ ሊያደልብለትም ይችላልና።
  3. ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "ችክ ብሎ ዱዓ ማድረግ፣ በአላህ ላይ ጥሩ እሳቤን ማሳደርና ተስፋ አለመቁረጥ ዱዓ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ከሚያደርጉ ትላልቅ ምክንያቶች መካከል ናቸው። ስለዚህም ሰውዬው ዱዓውን ችክ ብሎ ሊያደርግ፤ በአላህ ላይ ያለው እሳቤን ሊያሳምር፤ አላህ ጥበበኛና አዋቂ እንደሆነ በማወቅ ለአንዳች ጥበብ ሲባል ዱዓውን መቀበልን ሊያፈጥን ለአንዳች ጥበብም ዱዓውን መቀበሉን ሊያዘገይ እንደሚችል መረዳት ይገባል። አላህ ጠያቂ ከጠየቀው የተሻለ ነገርም ይሰጣል።"