ንዑስ ምድቦች

የሓዲሦች ዝርዝር

ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ አላህ ሆይ! ከፈለግክ ማረኝ! ከፈለግክ እዘንልኝ! ከፈለግክ ሲሳይን ለግሰኝ! አይበል። ጥያቄውን ቁርጥ ያድርግ። እርሱ አላህ የሻውን ይሰራልና። ለርሱም አስገዳጅ የለውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ