عَنْ عَائِشَةَ رضي الله عنها قَالَتْ:
كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَسْتَحِبُّ الْجَوَامِعَ مِنَ الدُّعَاءِ، وَيَدَعُ مَا سِوَى ذَلِكَ.
[صحيح] - [رواه أبو داود وأحمد] - [سنن أبي داود: 1482]
المزيــد ...
ከምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 1482]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የዱንያንም ሆነ የመጪውን አለም መልካም ነገር የጠቀለለ አላህ ላይ ማወደስና መልካም ፍላጎቶችንም ያካተተ ሁኖ ቃሉ አንሶ ሀሳቡ የበዛ ዱዓን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለንም ይተዉ ነበር።