عَنْ عَلِيٍّ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ مُكَاتَبًا جَاءَهُ، فَقَالَ: إِنِّي قَدْ عَجَزْتُ عَنْ مُكَاتَبَتِي فَأَعِنِّي، قَالَ: أَلاَ أُعَلِّمُكَ كَلِمَاتٍ عَلَّمَنِيهِنَّ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، لَوْ كَانَ عَلَيْكَ مِثْلُ جَبَلِ صِيرٍ دَيْنًا أَدَّاهُ اللَّهُ عَنْكَ، قَالَ:
«قُلْ: اللَّهُمَّ اكْفِنِي بِحَلاَلِكَ عَنْ حَرَامِكَ، وَأَغْنِنِي بِفَضْلِكَ عَمَّنْ سِوَاكَ».
[حسن] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 3563]
المزيــد ...
ከዓሊይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «አንድ ነፍሱን ገንዘብ ከፍሎ ነፃ ለማውጣት ከአለቃው ጋር የተዋዋለ ባሪያ ወደርሱ መጣና እንዲህ አለው: "እኔ ነፍሴን ከፍዬ ነፃ የማወጣበት ገንዘብ ስላቃተኝ አግዘኝ።" ዐሊይም እንዲህ አለ: "በአንተ ላይ የሲር ተራራን የሚያህል እዳ ቢኖርብህ እንኳ አላህ እንዲከፍልልህ የሚያደርግን የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ያስተማሩኝን ቃላቶች ላስተምርህን?" እንዲህ ብለዋል:
‹እንዲህ በል: አልላሁመክፊኒ ቢሐላሊከ ዐን ሐራሚክ፤ ወአግኒኒ ቢፈድሊከ ዓመን ሲዋክ›"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በሐላልህ ከሐራምህ ጠብቀኝ፤ በችሮታህም ከአንተ ውጪ ካሉ አብቃቃኝ።" ማለት ነው።
[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3563]
አንድ ከአለቃው ጋር ነፍሱን ለመግዛትና ነፃ ሊያወጣት ተስማምቶ የተፃፃፈ ነገር ግን ገንዘብ የሌለው ባሪያ ወደ አማኞች አዛዥ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - መጣና እንዲህ አለ: "እኔ ያለብኝን ገንዘብ መክፈል አቅቶኛልና ገንዘቡን በመክፈል ላይ ወይም መፍትሄ የሚሆነኝን በማስተማርና በመጠቆም ላይ አግዘኝ።" የአማኞች አዛዥም እንዲህ አለው: "ጦይእ አካባቢ ውስጥ የሚገኘው የሲር ተራራን የሚያህል እዳ ቢኖርብህ እንኳ አላህ እዳህን ለሚገባው አካል በመክፈል ከመዋረድ እንድትድን የሚያደርግን የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ያስተማሩኝን ቃላቶች ላስተምርህን?" ቀጥሎ እንዲህ አለው: "እንዲህ በል (አልላሁመ ክፊኒ) አላህ ሆይ አርቀኝ፣ አዙረኝ (ቢሐላሊከ) በሐላልህ ተብቃቅቼ (ዐንሐራሚክ) ክልክልህ ላይ ከመውደቅ (ወአግኒኒ) አብቃቃኝ (ቢፈድሊከ) በቸርነትህ (ዐመንሲዋክ) ከአንተ ውጪ ካሉ ፍጡራን።