عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: لَا أَقُولُ لَكُمْ إِلَّا كَمَا كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ: كَانَ يَقُولُ:
«اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ وَالْجُبْنِ وَالْبُخْلِ وَالْهَرَمِ وَعَذَابِ الْقَبْرِ، اللهُمَّ آتِ نَفْسِي تَقْوَاهَا، وَزَكِّهَا أَنْتَ خَيْرُ مَنْ زَكَّاهَا، أَنْتَ وَلِيُّهَا وَمَوْلَاهَا، اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ عِلْمٍ لَا يَنْفَعُ، وَمِنْ قَلْبٍ لَا يَخْشَعُ، وَمِنْ نَفْسٍ لَا تَشْبَعُ، وَمِنْ دَعْوَةٍ لَا يُسْتَجَابُ لَهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2722]
المزيــد ...
ከዘይድ ቢን አርቀም - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኔ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይሉ ከነበሩት ውጪ አልልም። እርሳቸው እንዲህ ይሉ ነበር:
"አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፤ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፤ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፤ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ።" (ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና ፣ ከመታከት ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስት ፣ ከመጃጀትና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም ዕውቀት፣ አንተን ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።")
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2722]
ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ መካከል "አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ።" ወደ አንተ እጠጋለሁ። "ከስንፍና" የሚጠቅመኝን መዘየድ ከማልችልበት "ከመታከት" የመስራት ፍላጎትን ከማጣት፤ ሰነፍ ማለት መዘየድ የማይችል ሲሆን መታከት ማለት ደግሞ መስራት አለመፈለግ ማለት ነው። "ከፈሪነት" መስራት ለሚገባኝ ወደ ፊት ከመሄድ ከመቆጠብ፤ "ከስስታምነት" መስጠት ግዴታዬ ከሆነ ከመሰሰት "ከእርጅና" ሰውነትን የሚያደክም ከሆነ መጃጀት "ከቀብር ቅጣት" እና ለቀብር ቅጣት ከሚዳርጉ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ። "አላህ ሆይ ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት!" መልካምን ለመስራትና ወንጀልን ለመተው ግጠማት። "ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት" ከአንተ ውጪ ነፍሴን የሚያፀዳ አንድም የለምና ነፍሴን ከውዳቂና ርካሽ ስነምግባር አፅዳት። "አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና።" የነፍሴን ጉዳይ የምትቆጣጠር፣ ጌታዋ፣ ባለቤቷና እርሷን የምትጣቅመው በአንተው ፀጋ ነውና። "አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ።" የኮኮብ እውቀት፣ የጥንቆላና የድግምት እውቀት አይነቱ ወይም ለመጪው አለም ከማይጠቅም እውቀት ወይም ከማይሰራበት እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ። "አንተን ከማይፈራ ልብም በአንተ እጠበቃለሁ።" ለአንተ ከማይዋደቅ፣ ለአንተ የማይረጋ፣ አንተን በማውሳት ከማይረጋጋ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ከማትጠግብ ነፍስ" አላህ በሰጣትና ከለገሳት ጥሩና ሐላል ሲሳይ ከማትብቃቃ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ተቀባይነት ከሌላት" ተመላሽ ከሆነች "ዱዓም" በአንተ እጠበቃለሁ።"