عن أنس بن مالك رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«يَسِّرُوا وَلَا تُعَسِّرُوا، وَبَشِّرُوا وَلَا تُنَفِّرُوا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 69]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 69]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ዓለማዊም ይሁን ዲናዊ በሆኑ ጉዳዮች ለሰዎች ማቅለልና ማግራራትን እንዲሁም እነርሱ ላይ አለማክበድን አዘዙ። ይህም ማግራራት አላህ በፈቀደውና በደነገገው ድንበር ውስጥ ሆኖ ነው።
ሰዎችን በመልካም ነገሮች በማበሰርና እነርሱን ከመልካም ነገሮች ባለማሸሽ ላይም አበረታቱ።