+ -

عَنْ سَلْمَانَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ رَبَّكُمْ حَيِيٌّ كَرِيمٌ، يَسْتَحْيِي مِنْ عَبْدِهِ إِذَا رَفَعَ يَدَيْهِ إِلَيْهِ أَنْ يَرُدَّهُمَا صِفْرًا».

[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه] - [سنن أبي داود: 1488]
المزيــد ...

ከሰልማን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።"»

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 1488]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓእ ስናደርግ እጅን ከፍ በማድረግ ላይ አነሳሱ። አላህ (ሐይዩን) እጅግ በጣም የሚያፍር፤ መስጠትን የማይተው፤ ለባሪያው የሚያስደስተውን የሚያደርግና የሚጎዳውን የሚያስቀርለት ነው። (ከሪሙን) ሳይጠየቅ የሚሰጥ ቸር ነው። ከተጠየቀ በኋላስ (እንዴት ሊመልሰው ይሆን)?! አማኝ ባሪያው ለዱዓ ሁለት እጆቹን አንስቶ ለምኖት ለርሱ ባዶ አድርጎ መመለስን ያፍራል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰው ልጅ ወደ አላህ ፈላጊነቱንና ባርነቱን ግልፅ ባደረገ ቁጥር ዱዓው ተቀባይነት ማግኘቱም ተስፋ የሚደረግና ቅርብ ይሆናል።
  2. ዱዓእ በማድረግ መነሳሳቱን፣ እጆችን ማንሳት ተወዳጅ እንደሆነና እጆችን ማንሳት የዱዓ ተቀባይነትን ከሚያስገኙ ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
  3. አላህ ለባሮቹ ያለው ቸርነትና እዝነት ስፋቱ መገለፁን ተረድተናል።