عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ أَخِي بَنِي مُجَاشِعٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَامَ فِينَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ذَاتَ يَوْمٍ خَطِيبًا، فَقَالَ: وَسَاقَ الْحَدِيثَ وَفِيهِ:
«وَإِنَّ اللهَ أَوْحَى إِلَيَّ أَنْ تَوَاضَعُوا حَتَّى لَا يَفْخَرَ أَحَدٌ عَلَى أَحَدٍ، وَلَا يَبْغِي أَحَدٌ عَلَى أَحَدٍ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2865]
المزيــد ...
የበኒ ሙጃሺዕ ወንድም ከሆነው ከዒያድ ቢን ሒማር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ኹጥባ ለማድረግ ተነሱ። ከተናገሯቸው ንግግሮች መካከልም:
"አንዱ በአንዱ ላይ በማይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን በማይተላለፍበት ልክ እንድትተናነሱ አላህ ወደኔ ራዕይ አውርዷል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2865]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለባልደረቦቻቸው ኹጥባ ለማድረግ ተነሱ። ከተናገሯቸው መካከልም: አላህ እንዲህ ብሎ ራዕይ ማውረዱን ተናገሩ: ሰዎች በዘራቸው ወይም በገንዘባቸው ወይም ከዛ ውጪ ባሉ ነገሮች አንዱ በአንዱ ላይ ልቅናን፣ ኩራትንና ክብርን ለራሱ በማድረግ ሳይፎክርና አንዱ በአንዱ ላይ ወሰን ሳይተላለፍ ለፍጥረታት ራሳቸውን ዝቅ በማድረግና ማንነታቸውን በማለዘብ እርስ በርሳቸው መተናነሳቸው ግዴታ ነው።