عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ أَكْثَرُ دُعَاءِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً، وَفِي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር' የሚለውን ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው ዓለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።)

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠቅላይ የሆኑ ዱዓዎችን ማድረግ ያበዙ ነበር። ከነርሱም መካከል: "አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር" የሚለው ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው አለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ይህ ዱዓ ጣፋጭ፣ ሰፊና ሐላል የሆነ ሲሳይን፣ መልካም ሚስትን፣ የአይን ማረፊያ የሆነ ልጅን፣ እረፍትን፣ ጠቃሚ ዕውቀትን፣ መልካም ስራንና የመሳሰሉትን ተወዳጅና ፍቁድ የሆኑ ተፈላጊዎችን ባጠቃላይ የዱንያ መልካም ነገሮችን እንዲሁም በቀብር ውስጥ፣ በሒሳብ መቆሚያ ስፍራና በእሳት ውስጥ ከሚያጋጥም ቅጣቶች ሰላም መሆንን፣ የአላህን ውዴታ ማግኘት፣ ዘውታሪ ፀጋ መጎናፀፍን፣ አዛኝ ወደሆነው ጌታ መቅረብን የመሰሉ የመጨረሻው አለም መልካም ነገሮችንም የሚያጠቃልል ዱዓ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል ጠቅላይ የሆኑ ዱዓዎችን ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. የተሟላ ዱዓ የሚባለው ሰውዬው በዱዓው ውስጥ ዱንያዊም አኺራዊም መልካም ጉዳዮችን የሰበሰበ እንደሆነ ነው።