+ -

عَنْ شَدَّادِ بْنِ أَوْسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«سَيِّدُ الِاسْتِغْفَارِ أَنْ تَقُولَ: اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لاَ إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي، فَإِنَّهُ لاَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ» قَالَ: «وَمَنْ قَالَهَا مِنَ النَّهَارِ مُوقِنًا بِهَا، فَمَاتَ مِنْ يَوْمِهِ قَبْلَ أَنْ يُمْسِيَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ، وَمَنْ قَالَهَا مِنَ اللَّيْلِ وَهُوَ مُوقِنٌ بِهَا، فَمَاتَ قَبْلَ أَنْ يُصْبِحَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6306]
المزيــد ...

ከሸዳድ ቢን አውስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲጝፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈጝፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየጝፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።' ማለትህ ነው።'" እንዲህም ብለዋል "በርሷ አምኖ ቀን ላይ ያላትና በዛው ቀን ከማምሸቱ በፊት የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው። በርሷ አምኖ ምሽት ላይ ያላትና ከማንጋቱ በፊት የሞተ ሰውም እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረሀኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።)

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6306]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምህረት የሚጠየቅበት የተለያዩ ቃላቶች እንዳሉና በላጩና ትልቁ አንድ ባሪያ እንዲህ ብሎ መጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ: "አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈጝፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየጝፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረህኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።) በቅድሚያ ባሪያው የአላህን ብቸኝነት ያረጋግጣል። አላህ ፈጣሪው፣ ምንም አጋር ሳይኖረው የሚያመልከው መሆኑን፤ ጥራት ለተገባው አላህ የገባውን በርሱ የማመንና ለርሱ ታዛዥ የመሆንን ቃልኪዳን በአቅሙ ልክ እንደሚወጣ ያረጋግጣል። በአቅሙ ልክ ቃሉን እንደሚወጣ የሚያረጋግጠውም አንድ ባሪያ ምንም ያክል በአምልኮ ላይ ቢቆም አላህ ያዘዘውን ሁሉ መፈፀም ስለማይችል ነው። ለተዋለለት ፀጋ የሚገባውን ምስጋናም ማቅረብ አይችልም። ወደ አላህም ይጠጋል፣ በርሱም ይጠበቃል፣ ባሪያ ከሰራው ክፋት መጠበቂያው አላህ ነውና። አላህ ለርሱ የዋለለትን ፀጋም በታዛዥነት ለርሱ ያረጋግጣል፤ እውቅናንም ይሰጣል። ወደ ነፍሱ በመመለስም ወንጀሉና ኃጢአቱን ያረጋግጣል፤ ያምናልም። በዚህ መልኩ ወደ አላህ ከተቃረበ በኋላ ጌታው እንዲምረው፣ ወንጀሎቹን እንዲሸሽግለት፣ በይቅር ባይነቱ፣ በችሮታውና እዝነቱ ከወንጀሎቹ እንዲጠብቀውም ዱዓ ያደርጋል። ምክንያቱም ከአላህ በቀርም ወንጀሎችን የሚምር የለምና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ዱዓ ከንጋትና ምሽት ውዳሴዎች መካከል መሆኗንና በቀኑ መጀመሪያ ፀሀይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ ወደ መግቢያዋ ዘንበል እስክትል ድረስ ባለው ወቅት ላይ በእርግጠኝነት፣ መልዕክቷን በማሰብ አምኖባት ካለ በኃላ የሞተ ሰው ጀነት የሚገባ መሆኑን ተናገሩ። በምሽትም ወቅት እርሱም ፀሀይ ከገባችበት አንስቶ ጎህ እስኪወጣ ድረስ ያለ ሰውና ከመንጋቱም በፊት የሞተ ጀነት ይገባል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ምህረትን የመጠየቂያ ቃላቶች የተለያዩ ሲሆኑ ከፊሉም ከከፊሉ ይበላለጣል።
  2. አንድ ባሪያ በዚህ ዱዓ አላህን ለመለመን መጓጓት ይገባዋል። ምክንያቱም የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲጝፋር) አለቃ ነውና።