عَنْ عَبْدِ اللهِ بنِ مَسعُودٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«عَلَيْكُمْ بِالصِّدْقِ، فَإِنَّ الصِّدْقَ يَهْدِي إِلَى الْبِرِّ، وَإِنَّ الْبِرَّ يَهْدِي إِلَى الْجَنَّةِ، وَمَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَصْدُقُ وَيَتَحَرَّى الصِّدْقَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللهِ صِدِّيقًا، وَإِيَّاكُمْ وَالْكَذِبَ، فَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وَإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، وَمَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَكْذِبُ وَيَتَحَرَّى الْكَذِبَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللهِ كَذَّابًا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2607]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ እውነተኛ ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ እውነት ከመናገርና እውነትን ከመምረጥ አይወገድም። አደራችሁን ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል። ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ ከመዋሸትና ለውሸት ከመጣር አይወገድ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2607]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እውነተኝነትን አዘዙ። እውነተኝነትን አጥብቆ መያዝ ለዘውታሪ መልካም ስራና በመልካም ስራ ላይም እንዲዘወትር የሚያደርገው በመሆኑ ሰውዬውን ወደ ጀነት እንደሚያደርሰው ተናገሩ። ሰውዬው እውነት መናገርን በድብቅም ይሁን በይፋ ከመደጋገም እስካልተወገደ እጅግ እውነተኛ የሚል ስያሜ እስኪገባው ይደርሳል። ይህም በእውነተኝነት ላይ ጫፍ የደረሰ ሰው ማለት ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከውሸትና ከቅጥፈት ንግግር አስጠነቀቁ። ይህም ከቀጥተኛው መንገድ ወደ መጣመም፣ ለክፋትና ለወንጀል ስለሚያነሳሳ ነው። ከዚያም ወደ እሳት ያደርሰዋል። ሰውዬውም ውሸትን ከማብዛት እስካልተወገደ ድረስ አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይፃፋል።