+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«كَلِمَتَانِ خَفِيفَتَانِ عَلَى اللِّسَانِ، ثَقِيلَتَانِ فِي الْمِيزَانِ، حَبِيبَتَانِ إِلَى الرَّحْمَنِ: سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيمِ، سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6406]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አርራህማን ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላቶች አሉ: ' 'ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6406]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰው ልጅ ያለምንም መጨናነቅና በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆኖ ስለሚናገራቸው ሁለት ቃላቶች ነገሩን። እነሱም ምንዳቸው ሚዛን ላይ የገዘፈ፣ ጌታችን አር‐ራሕማንም የሚወዳቸው ናቸው።
"ሱብሓነላሂ አልዐዚም ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ" የሚሉት ናቸው። ደረጃቸው የላቀበትም ምክንያት የአላህን የልቅናና የምሉዕነት ባህሪያት የያዙ ፤ የላቀውንና የጠራውን አላህንም ከጉድለቶች ስለሚያጠሩ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በላጩ ውዳሴ አላህን ማጥራትና ማወደስን የሰበሰበ ውዳሴ ነው።
  2. አላህ በጥቂት ስራ ብዙ ምንዳ መመንዳቱ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን ይገልፅልናል።