+ -

عَنْ جُوَيْرِيَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خَرَجَ مِنْ عِنْدِهَا بُكْرَةً حِينَ صَلَّى الصُّبْحَ، وَهِيَ فِي مَسْجِدِهَا، ثُمَّ رَجَعَ بَعْدَ أَنْ أَضْحَى، وَهِيَ جَالِسَةٌ، فَقَالَ: «مَا زِلْتِ عَلَى الْحَالِ الَّتِي فَارَقْتُكِ عَلَيْهَا؟» قَالَتْ: نَعَمْ، قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَقَدْ قُلْتُ بَعْدَكِ أَرْبَعَ كَلِمَاتٍ، ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَوْ وُزِنَتْ بِمَا قُلْتِ مُنْذُ الْيَوْمِ لَوَزَنَتْهُنَّ: سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ، عَدَدَ خَلْقِهِ وَرِضَا نَفْسِهِ وَزِنَةَ عَرْشِهِ وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2726]
المزيــد ...

የአማኞች እናት ከሆነችው ከጁወይሪያ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው:
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱብሒን የሰገዱ ጊዜ እርሷ መስገጃዋ ላይ ሆና ሳለ በማለዳ ከርሷ ዘንድ ወጡ። ከዚያም ከረፈደ በኋላ እርሷ (መስገጃዋ ዘንድ) ተቀምጣ ሳለ ተመለሱ። እንዲህም አሏት "እስካሁን ቅድም በነበርሸረበት ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" እርሷም "አዎን" አለች። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሏት "ከአንቺ ጋር ከተለያየሁ በኋላ ሶስት ጊዜ አራት ንግግሮችን ተናግሬያለሁ። እነዚህ አራት ንግግሮች አንቺ ከንጋት ጀምሮ ካልሻቸው ጋር ቢመዘን (የኔ አራቱ ቃሎች) ሚዛን ይደፋሉ።" ሱብሓነሏህ ወቢሐምዲሂ፣ ዐደደ ኸልቂሂ፣ ወሪዷ ነፍሲሂ፣ ወዚነተ ዐርሺሂ ወሚዳደ ከሊማቲህ" አሏት።» ትርጉሙም "አላህ የፈጠራቸውን ፍጡራን ቁጥር ያህል፣ የነፍሱ ውዴታን ያህል፣ ዐርሹ የሚመዝነውን ያህል፣ የንግግሩ መጠን ያህል ከምስጋና ጋር ጥራት ይገባው።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2726]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሱብሒን ከሰገዱ በኋላ የአማኞች እናት ከሆነችው ከባለቤታቸው ጁወይሪያ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) ዘንድ እርሷ መስገጃ ስፍራዋ ላይ ተቀምጣ ሳለ የንጋቱ መጀመሪያ ላይ ወጡ። ከዚያም ንጋቱ ከተጋመሰ በኋላ በረፋድ ወቅትም ተመለሱ። እርሷም በነበረችበት ቦታ ላይ ከመቀመጥ አልተወገደችም ነበር። እንዲህም አሏት: እስካሁን ስለያይሽ የነበርሽበት ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽምን? እርሷም "አዎን" አለች። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: ከአንቺ ጋር ከተለያየሁ በኋላ ሶስት ጊዜ ደጋግሜ አራት ንግግሮችን ተናግሬያለሁ። እነዚህ አራት ንግግሮች አንቺ በተቀምጠሽበት ጊዜ ባጠቃላይ ካልሻቸው አዝካሮች ጋር ቢወዳደር ከምንዳ አንፃር እነዚህ አራት ቃላቶች ሚዛን ይደፋሉ። (ሱብሓነሏህ) ከሁሉም ጉድለቶች አላህ ጥራት የተገባው ነው። (ወቢሐምዲሂ) ለዚህ ስለመራንም መልካም ውዳሴ የተገባው ነው። (ዐደደ ኸልቂህ) ቁጥራቸውን ከአላህ በቀር ማንም የማያውቃቸው ፍጡራኑን ያህል (ወሪዷ ነፍሲህ) አላህ ከባሮቹ መካከል ውዳሴውን የወደደለትን ሰው ከርሱ በወደደለት ልክ። ይህም ከርሱ በቀር ማንም የማያካበው ነው። (ወዚነተ ዐርሺህ) ትልቁና ከባዱ ፍጡሩ የሆነው የዐርሽ ክብደት ያህል (ወሚዳደ ከሊማቲህ) የአላህ ንግግር ያህል። የአላህ ንግግር በቁጥር የማይዘለቁና የማያልቁ ናቸው። ይህም ሶስቱንም ክፍሎች ያጠቃልላል። የአላህ ንግግር መጠኑም፣ መገለጫውም፣ ቁጥሩም መጨረሻ የለውም። ነገር ግን በዚህ ንግግራቸው ማለት የፈለጉት ብዛቱን ወሰን የለሽ ለማድረግ ነው። በመጀመሪያ በብዙ ቁጥር ውስጥ የሚካተትን ነገር ገለፁ። እርሱም የፍጡራኑ መጠን ነው። ቀጥለው ከዛም ከፍ ወዳለ አለፉ። እርሱም በነፍሱ ውዴታ መግለፃቸው ነው። ከዚያም ከፍጡራኖቹ ሁሉ በከባድ የሚመዝነው ነው። እርሱም በዐርሽ መግለፃቸው ነው። የመጀመሪያውን ከመጠን አንፃር፣ ሁለተኛው ከሁኔታና ባህሪ አንፃር ሶስተኛውን ደግሞ ከትልቀትና ክብደት አንፃር ገለፁበት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የነዚህ ንግግሮች ደረጃ መገለፁና እነዚህን ንግግሮች በመናገር ላይ መነሳሳቱን (መበረታታቱን) እንረዳለን።
  2. ዚክር ይበላለጣል። አንዳንዶቹ ዚክሮች ከሌሎቹ ዚክሮች ይበልጣሉ።
  3. ነወዊይ (ሱብሓነሏህ ወቢሐምዲሂ ሚዳደ ከሊማቲህ) የሚለውን በማስመልከት እንዲህ ብለዋል: የተፈለገው ብዛቱን ከፍ አድርጎ ለመግለፅ ነው። እርሳቸው መጀመሪያ በብዙ ቁጥር ውስጥ በሚካተት መልኩ ገለፁ። እርሱም የፍጡራኑ መጠን ነው። ቀጥለው የዐርሽን ክብደት ገለፁ። ከዚያም ከነዚህም ወደሚልቀው አለፉና በዚህ መልኩ ገለፁት። ማለትም በቁጥር የማይዘለቀው የሆነው ንግግርህን ያህል ከማመስገን ጋር አጠራሃለው ማለት ነው።
  4. ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ብለዋል: "አንድ ዚክር የሚል ሰው "ሱብሓነሏህ ወቢሐምዲሂ ዐደደ ኸልቂሂ ......" እያለ እስከመጨረሻው በሚልበት ጊዜ ቀልቡ ይሄን የተጠቀሰውን ቁጥር ያህል አላህን በማወቅ፣ በማጥራትና በማላቅ የምትላበሰው ሁኔታ "ሱብሓነሏህ" ብቻ የሚል ሰው ቀልቡ ከምትላበሰው ሁኔታ የላቀ ነው።
  5. ጥቂት ቃላትን በመጠቀም በርሷ ግን ትልቅ ምንዳና ደረጃ የሚያሰጡ የሆኑ ጠቅላይ ቃላቶች አስፈላጊነታቸውን ተረድተናል።