+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«لَيْسَ شَيْءٌ أَكْرَمَ عَلَى اللهِ تَعَالَى مِنَ الدُّعَاءِ».

[حسن] - [رواه الترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 3370]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካምስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል:
"ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"

[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3370]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአምልኮዎች መካከል ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ እጅግ በላጭ የሆነ አምልኮ አንድም እንደሌለ ገለፁ። ምክንያቱም ዱዓእ የአላህን መብቃቃት፣ የባሪያን ደካማነትና ፈላጊነት እውቅና መስጠትን ውስጡ ይዟልና ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የዱዓእን ትሩፋት እንረዳለን። አላህን የለመነ ሰው አላህን እያላቀ፣ የሌለው አይከጀልምና ጥራት የተገባው አምላክ እጅግ የተብቃቃ መሆኑን፣ ደንቆሮ አይለመንምና እጅግ ሰሚ መሆኑን፣ ስስታም አይለመንምና ቸር መሆኑን፣ ልበደረቅ አይለመንምና አዛኝ መሆኑን፣ ደካማ አይለመንምና ቻይ መሆኑን፣ ሩቅ ያለ አይሰማምና ቅርብ መሆኑን እና ሌሎችም የልቅናና የምሉዕነት መገለጫዎችን ለአሏህ እያረጋገጠ ነው።