عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا جَلَسَ قَوْمٌ مَجْلِسًا لَمْ يَذْكُرُوا اللَّهَ فِيهِ وَلَمْ يُصَلُّوا عَلَى نَبِيِّهِمْ إِلاَّ كَانَ عَلَيْهِمْ تِرَةً، فَإِنْ شَاءَ عَذَّبَهُمْ وَإِنْ شَاءَ غَفَرَ لَهُمْ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى] - [سنن الترمذي: 3380]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች አላህን ያላወሱበትና በነቢያቸው ላይ ሶላት ያላወረዱበት መቀማመጥ ከተቀመጡ በነርሱ ላይ ቁጭት ይሆንባቸዋል። ከፈለገ ይቀጣቸዋል ከፈለገም ይምራቸዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን ቲርሚዚ - 3380]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህን ከማውሳት ከመዘናጋት አስጠነቀቁ። እርሱም ሰዎች አላህን በርሱ ያላወሱበትና በመልክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶላት ያላወረዱበት መቀማመጥ ከተቀመጡ ይህ መቀማመጥ የትንሳኤ ቀን በነርሱ ላይ ቁጭት፣ ፀፀት፣ ክስረትና ጉድለት ይሆንባቸዋል። ከፈለገ አላህ በቀደመ ወንጀላቸውና ባለባቸው ጉድለት ምክንያት ይቀጣቸዋል። ከፈለገም በችሮታውና በእዝነቱ ለነርሱ ይምራቸዋል።