+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ رَفَعَهُ:
فِي قَوْلِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ: {وَمَنْ يُرِدْ فِيهِ بِإِلْحَادٍ بِظُلْمٍ نُذِقْهُ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ} [الحج: 25] قَالَ: «لَوْ أَنَّ رَجُلًا هَمَّ فِيهِ بِإِلْحَادٍ وَهُوَ بِعَدَنِ أَبْيَنَ لَأَذَاقَهُ اللَّهُ عَذَابًا أَلِيمًا».

[صحيح] - [رواه أحمد والحاكم] - [المستدرك على الصحيحين: 3461]
المزيــد ...

ዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዳስተላለፈው
{በእርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ) በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።} [አልሐጅ: 25] በሚለው የአላህ ንግግር ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰውዬ ዓደን አብየን ላይ ሆኖ እንኳ ሐረም ውስጥ በደል ለመስራት ቢያስብ አላህ አሳማሚ ቅጣትን ያቀምሰዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] - - [አልሙስተድረክ ዓለስሶሒሐይን - 3461]

ትንታኔ

ዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - {በእርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ) በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።} [አልሐጅ: 25] በሚለው የአላህ ቃል ዙሪያ እንዲህ ማለታቸውን ገለፀ: "አንድ ሰው በሐረም መካ ላይ በምላስ ወይም ሆን ብሎ በመግደል አላህ እርም ያደረገው በሚደፈርበት መልኩ መጥፎን ስራ ለመስራት በነፍሱ ቢያስብና ቢቆርጥ ይህን ሊያደርግ የቆረጠው በየመን ከሚገኘው የዓደን ከተማ ሆኖ ቢሆንና ባይሰራው እንኳ በዚህ ምክንያት አላህ በአሳማሚ ቅጣቱ ሊቀጣው የተገባ ይሆናል። ለዚህ ቅጣት ማሰቡ ብቻ በቂ ነው።"

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሐረም ልዩ ስፍራና የላቀ መሆኑን መገለፁ እንረዳለን።
  2. ሰዕዲይ እንዲህ ብለዋል: "በዚህች በተከበረች አንቀፅ ሐረምን ማክበርና እጅግ ማላቅ ግዴታ መሆኑን፤ እንዲሁም ሐረም ውስጥ ሆኖ ወንጀል ማሰብና መስራት መከልከሉን እንረዳለን።"
  3. ዶሐክ እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው ሌላ ምድር ላይ ሆኖ መካ ላይ ወንጀል ለመስራት ቢያስብና ግን ወንጀሉን ባይሰራው እንኳ በርሱ ላይ ወንጀል ይፃፍበታል።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ