عَنْ جَابِرٍ رَضيَ اللهُ عنهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ قَالَ: سُبْحَانَ اللهِ العَظِيمِ وَبِحَمْدِهِ، غُرِسَتْ لَهُ نَخْلَةٌ فِي الجَنَّةِ».
[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 3464]
المزيــد ...
ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሱብሓነሏሂል ዐዚም ወቢሐምዲሂ ያለ ሰው ጀነት ውስጥ ለርሱ የተምር ዛፍ ይተከልለታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3464]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና (ሱብሓነሏሂ) አላህ ጥራት የተገባው ነው። (አልዐዚም) በዛቱ፣ በባህሪያቱና በድርጊቱ ታላቅ ነው። (ወቢሐምዲህ) የምሉዕነት መገለጫዎቹን ማስጠጋት አቆራኝቼ አጠራዋለሁ ያለ ሰው ይህቺን ውዳሴ ባለ ቁጥር በጀነት መሬት ላይ የተምር ዛፍ ይተከልለታል አሉ።