+ -

لَقِيتُ ثَوْبَانَ مَوْلَى رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقُلْتُ: أَخْبِرْنِي بِعَمَلٍ أَعْمَلُهُ يُدْخِلُنِي اللهُ بِهِ الْجَنَّةَ؟ أَوْ قَالَ قُلْتُ: بِأَحَبِّ الْأَعْمَالِ إِلَى اللهِ، فَسَكَتَ. ثُمَّ سَأَلْتُهُ فَسَكَتَ. ثُمَّ سَأَلْتُهُ الثَّالِثَةَ فَقَالَ: سَأَلْتُ عَنْ ذَلِكَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: @«عَلَيْكَ بِكَثْرَةِ السُّجُودِ لِلَّهِ، فَإِنَّكَ لَا تَسْجُدُ لِلَّهِ سَجْدَةً، إِلَّا رَفَعَكَ اللهُ بِهَا دَرَجَةً، وَحَطَّ عَنْكَ بِهَا خَطِيئَةً»* قَالَ مَعْدَانُ: ثُمَّ لَقِيتُ أَبَا الدَّرْدَاءِ فَسَأَلْتُهُ فَقَالَ لِي: مِثْلَ مَا قَالَ لِي: ثَوْبَانُ.
[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«የአላህ መልክተኛ ነፃ ወጪ ባሪያ የነበረውን ሠውባንን አገኘሁትና እንዲህ አልኩት: አላህ በርሱ ጀነት እንድገባ የሚያደርግብኝን የምሰራውን ስራ ንገረኝ? ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ስራ ንገረኝ? እርሱም ዝም አለ። በድጋሚ ጠየቅኩት አሁንም ዝም አለ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቅኩት እርሱም: "ስለዚህ ጉዳይ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"» መዕዳን እንዲህ አለ «ቀጥሎ አቡ ደርዳእን አገኘሁና ጠየቅኩት። እርሱም ሠውባን ያለኝን አምሳያ ነገረኝ።»

ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀነት ለመግባት ሰበብ ስለሆነ ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስለሆነ ስራ ተጠየቁ።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጠያቂው እንዲህ አሉት: ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማብዛትን አዘውትር! አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም ቢምርህ እንጂ አንድም ሱጁድ ለአላህ አትወርድም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ السويدية القيرقيزية اليوروبا الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶላት ሱጁድን ስለሚያካትት ግዴታም ሆነ ሱና ሶላት ለመስገድ ጥረት በማድረግ ላይ ሙስሊሞች መበረታታታቸው፤
  2. የሶሐቦች ግንዛቤና እውቀት መገለፁ። ይህም ጀነት ከአላህ እዝነት በኋላ በስራ ካልሆነ በቀር እንደማትገኝ ማወቃቸው ነው።
  3. ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማድረግ ደረጃን ከፍ ለማድረግና ወንጀሎችን ለማስማር ትልቁ ምክንያት ነው።
ተጨማሪ