عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«يَعْقِدُ الشَّيْطَانُ عَلَى قَافِيَةِ رَأْسِ أَحَدِكُمْ إِذَا هُوَ نَامَ ثَلاَثَ عُقَدٍ يَضْرِبُ كُلَّ عُقْدَةٍ عَلَيْكَ لَيْلٌ طَوِيلٌ، فَارْقُدْ، فَإِنِ اسْتَيْقَظَ فَذَكَرَ اللَّهَ، انْحَلَّتْ عُقْدَةٌ، فَإِنْ تَوَضَّأَ انْحَلَّتْ عُقْدَةٌ، فَإِنْ صَلَّى انْحَلَّتْ عُقْدَةٌ، فَأَصْبَحَ نَشِيطًا طَيِّبَ النَّفْسِ، وَإِلَّا أَصْبَحَ خَبِيثَ النَّفْسِ كَسْلاَنَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1142]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ የተኛ ጊዜ በማጅራቱ ላይ ሸይጧን ሶስት ቋጠሮ ይቋጥራል። በየሁሉም ቋጠሮ ላይም ረጅም ሌሊት አለና ተኛ! እያለ ይመታል። ከነቃና አላህን ካወሳ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ዉዱእ ካደረገ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ከሰገደ ደግሞ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ያኔ ንቁና ነፍሱ የተደሰተች ሆኖ ያነጋል። ያለበለዚያ ግን ነፍሱ የከበደችውና የሰነፈ ሆኖ ያነጋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1142]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሸይጧን ሌሊት ለመስገድ ወይም ፈጅርን ለመስገድ መቆም ከፈለገ ሰው ጋር ያለውን ሁኔታና ግብግብ ነገሩን።
አማኝ ለመተኛት የሄደ ጊዜ ሸይጧን ማጅራቱ ላይ ሶስት ቋጠሮ ይቋጥርበታል።
አማኙ ነቅቶ አላህን ካወሳና ለሸይጧን ጉትጎታ እጅ ካልሰጠ አንዷ ቋጠሮ ትፈታለች።
ዉዱእ ካደረገ ደሞ ሌላኛዋ ቋጠሮ ትፈታለች ።
ቆሞ ከሰገደ ሶስተኛው ቋጠሮ ይፈታል። የሸይጧን ቋጠሮና ማዳከም ከመወገዱ በተጨማሪ አላህ ለአምልኮ ስለገጠመው በመደሰትና አላህ ቃል በገባለት ምንዳና ምህረት በመበሰር ንቁና ነፍሱም የተደሰተች ይሆናል። ያለበለዚያ ግን ነፍሱ የከበደችው፣ ቀልቡ ያዘነና ከመልካምና በጎ ስራ የተሳነፈ ይሆናል። ምክንያቱም እርሱ በሸይጧን ገመድ የታሰረና ወደ አር‐ራሕማን ከመቅረብ የራቀ ስለሆነ ነው።