+ -

عَنِ الْعَبَّاسِ بْنِ عَبْدِ الْمُطَّلِبِ رضي الله عنه أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، يَقُولُ:
«ذَاقَ طَعْمَ الْإِيمَانِ مَنْ رَضِيَ بِاللهِ رَبًّا، وَبِالْإِسْلَامِ دِينًا، وَبِمُحَمَّدٍ رَسُولًا».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 34]
المزيــد ...

ከዓባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማቸው:
"በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖት እና የነብዩ ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 34]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኢማኑ ላይ እውነተኛ አማኝ የሆነና ልቡ በኢማን የተረጋጋ ሰው እነዚህን ሶስት ነገሮች ከወደደ ልቡ ውስጥ መስፋት፣ መደሰት፣ ማጣጣም እንደሚሰማውና ወደ አላህ የመቅረብን እርካታ እንደሚያገኝ ተናገሩ።
የመጀመሪያው: በአላህ ጌትነት መውደድ ነው። ይህም በርሱ ላይ የአላህን ጌትነቱን የሚያስፈርዱ ሲሳይ ማከፋፈልና ሁኔታዎችን መወሰን ሲከሰትበት ልቡ ውስጥ አንዳችም ተቃውሞ አያገኝምም፤ ከአላህ ውጪ ጌታንም አይፈልግም።
ሁለተኛ: በእስልምና ሃይማኖት መውደድ ነው። ይህም እስልምና ላካተታቸው ሀላፊነቶችና ግዴታዎች ልቡን መክፈቱና ከእስልምና መንገድ ውጪ ላለ ሃይማኖት ልቡን አለመክፈቱ ነው።
ሶስተኛ: በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መልክተኝነት መውደድ ነው። ይህም እርሳቸው ይዘውት ላመጡት ነገር ባጠቃላይ ምንም ሳይጠራጠርና ሳያወላውል ልቡን መክፈትና መደሰት፤ የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ የገጠመውን ካልሆነ በቀር ላያደርግ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የምግብና የመጠጥ ጣዕም ጥፍጥና በአፍ እንደሚቀመሰው ኢማንም በቀልብ የሚቀመስ የሆነ ጥፍጥናና ጣዕም እንዳለው እንረዳለን።
  2. ሰውነት የምግብና የመጠጥ ጣዕም ጥፍጥና የሚሰማው ጤነኛ ሲሆን ነው። ልክ እንደዚሁ ቀልብ ከአጥማሚ ዝንባሌና ክልክል ስሜቶች በሽታ ሲነፃ የኢማንን ጥፍጥና ያገኛል። ቀልብ ከታመመና ከተጎዳ ግን የኢማንን ጥፍጥና ሳይሆን የሚያገኘው መጥፊያው የሆነ ወንጀልና ዝንባሌ ነው የሚጣፍጠው።
  3. የሰው ልጅ አንድን ነገር ከወደደና መልካም ካደረገው ነገሮች ይገሩለታል። አንድም ነገሩ አይከብደውም። ከርሱ በሚመጣ ነገር ባጠቃላይም ይደሰታል። የሚያስደስተው ነገር ነፀብራቅ ቀልቡን ይቀላቀለዋል። ልክ እንደዚሁ አንድ አማኝ ኢማን ቀልቡ ውስጥ የገባ ጊዜ ጌታውን መታዘዝ ይገራለታል፣ ነፍሱም በዚህ ትደሰታለች፣ እርሷን ማከምም አይከብደውም።
  4. ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ በአላህ ጌትነትና ተመላኪነት መውደድን፣ በመልክተኛውና ለርሳቸው በመታዘዝ መውደድን፣ በሃይማኖቱና ለርሱ እጅ መስጠቱን መውደድን አካቷል።»
ተጨማሪ