عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو رضي الله عنهما قال: قال رَسولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَرْبَعٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ كَانَ مُنَافِقًا خَالِصًا، وَمَنْ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْهُنَّ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْ نِفَاقٍ حَتَّى يَدَعَهَا: إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ، وَإِذَا عَاهَدَ غَدَرَ، وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ، وَإِذَا خَاصَمَ فَجَرَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 58]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ጥርት ያለ ሙናፊቅ ይሆናል። ከነርሱ መካከል ከፊሉ ያለበት ሰው እስኪተወው ድረስ ከፊል ንፍቅና ይኖርበታል። ሲያወራ ይዋሻል፣ ቃልኪዳን ይዞ ያፈርሳል፣ ቀጠሮ ይዞ ያፈርሳል፣ ሲሟገት (ድንበር ያልፋል) በጥመት ላይ ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 58]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች አስጠነቀቁ። እነዚህ አራት ነገሮች አንድ ሙስሊም ላይ የተሰባሰቡ ጊዜ በነዚህ ነገሮች ሰበብ ከመናፍቃን ጋር እጅግ በጣም ይመሳሰላል። ይህ ግን እነዚህ አራት ነገሮች እርሱ ላይ በብዛት የሚስተዋሉ ከሆነ ነው እንጂ አልፎ አልፎ የሚስተዋልበት ከሆነ ግን እዚህ ውስጥ አይካተትም። እነሱም:-
የመጀመሪያው: ሲያወራ ሆን ብሎ ይዋሻል፣ በንግግሩም እውነቱን አይናገርም።
ሁለተኛ: አንድ ቃል ኪዳን ከገባ ቃልኪዳኑን አይሞላም። ቃልኪዳን ለገባለት ሰውም ቃሉን ያፈርሳል።
ሶስተኛ: ቀጠሮን የቀጠረ ጊዜ የገባውን ቃል አይሞላም። ቀጠሮውን ያፈርሳል።
አራተኛ: ከአንድ ሰው ጋር የተጨቃጨቀና የተሟገተ ጊዜ ሙግቱ ሀይለኛ ይሆናል። ከእውነትም ይዘነበላል። እውነትን ላለመቀበልም በተንኮል ጥመትና ውሸትን ይናገራል።
ንፍቅና ማለት ውስጡ ካለው ተቃራኒ የሆነን ነገር ግልፅ ማውጣት ነው። የዚህ ሀሳብም በተመሳሳይ እነዚህን ነገሮች በሚተገብር ላይ ይገኛሉ። ንፍቅናውም ባዋራው፣ በቀጠረው፣ ባመነው፣ በተከራከረውና ቃልኪዳን በገባለት ሰው ሐቅ ላይ ነው እንጂ እስልምናን ግልፅ እያደረገ ክህደትን በመደበቅ በእስልምና ላይ መናፍቅ ሆኗል ማለት አይደለም። ከነዚህ ነገሮች መካከል አንድ ጉዳይ ያለበትም እስኪተወው ድረስ በርሱ ላይ የንፍቅና ባህሪ አለበት።