+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ أَوَّلَ زُمْرَةٍ يَدْخُلُونَ الجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ القَمَرِ لَيْلَةَ البَدْرِ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ عَلَى أَشَدِّ كَوْكَبٍ دُرِّيٍّ فِي السَّمَاءِ إِضَاءَةً، لاَ يَبُولُونَ وَلاَ يَتَغَوَّطُونَ، وَلاَ يَتْفِلُونَ وَلاَ يَمْتَخِطُونَ، أَمْشَاطُهُمُ الذَّهَبُ، وَرَشْحُهُمُ المِسْكُ، وَمَجَامِرُهُمْ الأَلُوَّةُ الأَنْجُوجُ، عُودُ الطِّيبِ وَأَزْوَاجُهُمُ الحُورُ العِينُ، عَلَى خَلْقِ رَجُلٍ وَاحِدٍ، عَلَى صُورَةِ أَبِيهِمْ آدَمَ، سِتُّونَ ذِرَاعًا فِي السَّمَاءِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3327]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው ስብስብ ጨረቃ ሙሉ የምትሆንበትን (የለይለቱል በድርን) አይነት ውበት ይዘው ነው። ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ የሚያበሩት ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ መስለው ነው። አይሸኑም፤ ሰገራም አይወጣቸውም፤ አይተፉም፤ አይናፈጡም። ማበጠሪያቸው ወርቅ ነው፤ ላባቸው ሚስክ ነው፤ እጣን ማጤሻቸው ምርጥ መአዛ ያለው እንጨት የ 'ኡሉወቱል አንጁጅ' ነው፤ ሚስቶቻቸው ሑሩል ዒን ናቸው። ጀነት ሲገቡ ልክ እንደ አንድ ሰው አፈጣጠር በአባታቸው አደም ቅርፅ ላይ ሆነው ነው የሚገቡት። ቁመታቸው ስልሳ ክንድ ሆነው ነው የሚገቡት።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3327]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው የአማኞች ህብረት ጨረቃ ሙሉ እንደምትሆንበት ምሽት ፊቶቻቸው እያበራ እንደሆነ፤ ከነርሱ ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ ውበታቸው ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ እንደሆነ፤ እንዲሁም የጀነት ሰዎች የተሟላ ባህሪያት እንዳላቸው ይህም የማይሸኑ፤ ሰገራ የማይወጣቸው፤ የማይተፉና የማይናፈጡ መሆናቸውን፤ ማበጠሪያቸውም ወርቅ፤ ላባቸው ሚስክ፤ ከእጣን ማጨሻቸው የሚወጣው መአዛ ምርጥ መአዛ ያለው እጣን እንደሆነ፤ ሚስቶቻቸው ሑሩል ዒን ናቸው። በአፈጣጠርና ቁመትም ልክ እንደ አንደሰው የአባታቸውን አደም ቅርፅ ይዘው እንዳላቸውና የአደም ሰውነት ርዝማኔም ስልሳ ክንድ እንደሆነ ተናገሩ።

ትርጉም: ኢንዶኔዥያኛ ቬትናማዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የጀነት ሰዎች ባህሪ መገለፁንና እነርሱም እንደየደረጃቸውና ስራዎቻቸው እንደሚበላለጡ ተረድተናል።
  2. ሀሳቦችን ለማስረዳትና ለማብራራት ምሳሌዎችን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
  3. ቁርጡቢ እንዲህ ብለዋል: "የጀነት ሰዎች ፂም የሌላቸውና ፀጉራቸውም የማይቆሽሽ ከመሆኑ ጋር ማበጠሪያ ለምን ያስፈልጋቸዋል? መአዛቸው ከሚስክ የበለጠ ምርጥ ሆኖ ሳለ እጣንስ ለምን ያስፈልጋቸዋል? የሚል ጥያቄ ከተነሳ: የጀነት ሰዎች ፀጋ መብላቱም፣ መጠጣቱም፣ መልበሱም፣ ሽቶውም በረሃብ ወይም በጥም ወይም በመራቆት ወይም በመቆሸሽ ህመም ምክንያት የሚጠቀሙት አይደለም። የጀነት ፀጋ የተከታተለ እርካታና የተነባበረ ፀጋ ስለሆነ ነው። የዚህም ጥበብ ዱንያ ላይ ይጣቀሙበት በነበረው አይነት እንዲጣቀሙ ነው። ተብሎ ይመለሳል።"