1. ዋና ገጽ
  2. ምድቦች
  3. ዐቂዳ (እምነት)

ሐዲሥ አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።

عَنْ عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«فِي الجَنَّةِ مِائَةُ دَرَجَةٍ مَا بَيْنَ كُلِّ دَرَجَتَيْنِ كَمَا بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ، وَالْفِرْدَوْسُ أَعْلاَهَا دَرَجَةً وَمِنْهَا تُفَجَّرُ أَنْهَارُ الجَنَّةِ الأَرْبَعَةُ، وَمِنْ فَوْقِهَا يَكُونُ العَرْشُ، فَإِذَا سَأَلْتُمُ اللَّهَ فَسَلُوهُ الفِرْدَوْسَ».

ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች አሉ። በየሁሉም ደረጃዎች መካከል በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ርቀት ያህል አለ። ፊርደውስ የላይኛው ደረጃ ነው። የጀነት ወንዞች የሚመነጩትም ከርሷ ነው። ከላዩዋ ያለውም (ጣሪያዋ) ዐርሽ ነው። አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።"

ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል። ሱነን ቲርሚዚ - 2531

ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመጪው አለም ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች እንዳሉ፤ በየሁሉም ደረጃዎች መካከል የሚገኘው ርቀት በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ያህል ርቀት እንደሆነ፤ ከነዚህ ጀነቶች መካከል ከፍተኛዋ ጀነት ፊርደውስ እንደሆነች፤ አራቱ የጀነት ወንዞች የሚመነጩትም ከርሷ መሆኑን፤ ከፊርደውስ በላይም ዐርሽ መሆኑንና ፊርደውስም ከሁሉም ጀነቶች በላይ ስለሆነች አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት ብለው ተናገሩ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. የጀነት ነዋሪዎች በደረጃ እንደሚበላለጡና ይህም በኢማንና በመልካም ስራዎቻቸው ልክ እንደሆነ እንረዳለን።
  2. አላህን ከጀነት ሁሉ ላእላይ የሆነችውን ፊርደውስ እንድንጠይቀው መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. ፊርደውስ የጀነት ላይኛዋና በላጯ እንደሆነች እንረዳለን።
  4. ሙስሊም የሆነ ሰው ከፍ ያለ አላማ ሊኖረው እንደሚገባና አላህ ዘንድ የላቀ የሆነንና በላጭ የሆነን ደረጃ ለማግኘት መልፋትና መጣር እንደሚገባው እንረዳለን።
  5. ጀነት አራት ወንዞች አሏት: እነርሱም: የውሃ፣ የወተት፣ ወይን ጠጅና የማር ናቸው። እነዚህም በዚህ የአላህ ንግግር ውስጥ በቁርአን ተጠቅሰዋል። {የዚያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ጀነት ምሳሌ በውስጧ ሽታውን ከማይለውጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከሆነች የወይን ጠጅም ወንዞች፣ ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት።} [ሙሐመድ: 15]

ትርጉሞችን አሳይ

40 ቋንቋ
EN English الإنجليزية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية