عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مِنْ حُسْنِ إِسْلَامِ المَرْءِ تَرْكُهُ مَا لَا يَعْنِيهِ».
[قال النووي: حديث حسن] - [رواه الترمذي وغيره] - [الأربعون النووية: 12]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦
“የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።"
[قال النووي: حديث حسن] - [رواه الترمذي وغيره] - [الأربعون النووية - 12]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የአንድ ሙስሊም እስልምና በተሟላ መልኩ የሚያምረውና ኢማኑ የሚሞላው ከማያገባው፣ ከማይመለከተው፣ ከማይጠቅመውና ከማያሳስበው ንግግርና ተግባር ወይም ከማይመለከተው ዲናዊና ዱንያዊ ጉዳይ ሲርቅ እንደሆነ ገለፁ። አንድ ሰው በማይመለከተው ነገር መጠመዱ ምናልባት ከሚጠቅመው ነገር ያዘናጋዋል ወይም መራቅ የሚገባውን ነገር እንዲፈፅም ይዳርገዋል። የሰው ልጅ የትንሳኤ ቀን ስለስራዎቹ ተጠያቂ ነውና።