+ -

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ أَنْ تُؤْتَى رُخَصُهُ، كَمَا يُحِبُّ أَنْ تُؤْتَى عَزَائِمُهُ».

[صحيح] - [رواه ابن حبان] - [صحيح ابن حبان: 354]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ግዴታ ያደረገው ሲተገበር እንደሚወደው፤ ያግራራውም ሲተገበር ይወዳል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ኢብኑ ሒባን - 354]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ አምልኮና ህግጋቶቹን በማቅለል የደነገጋቸው ማግራሪያዎች ሲተገበሩ እንደሚወድ ተናገሩ። እንዲሁም አቅመ አዳምና ጤነኛ የሆኑ ሰዎች በተቸገሩ ሰዓት የደነገገላቸውን ማቅለያዎች ለምሳሌ፦ ጉዞ ላይ ሰላትን ማሳጠርና ሰላትን ሰብስቦ መስገድ ይመስል ሲፈጸሙም አላህ እንደሚወድ ተናገሩ። ይህም ልክ ግዴታ ያደረጋቸው ሲሰሩ (ተግባራዊ ሲደረጉ) እንደሚወደው ነው። ምክንያቱም አላህ ባግራራውም ጉዳዮች ሆነ ግዴታ ባደረገው ጉዳዮች ላይ ትእዛዙ አንድ ነውና።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ጥራት የተገባው አላህ የደነገጋቸው ማግራሪያዎች ሲሰሩ መውደዱ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን እዝነት እንረዳለን።
  2. የዚህን ሸሪዐ ምሉእነትና በሙስሊም ላይ ችግርን ያነሳ መሆኑን እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ