عن النُّعمان بن بَشير رضي الله عنه قال: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ -وَأَهْوَى النُّعْمَانُ بِإِصْبَعَيْهِ إِلَى أُذُنَيْهِ-:
«إِنَّ الْحَلَالَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ، وَبَيْنَهُمَا مُشْتَبِهَاتٌ لَا يَعْلَمُهُنَّ كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ، فَمَنِ اتَّقَى الشُّبُهَاتِ اسْتَبْرَأَ لِدِينِهِ وَعِرْضِهِ، وَمَنْ وَقَعَ فِي الشُّبُهَاتِ وَقَعَ فِي الْحَرَامِ، كَالرَّاعِي يَرْعَى حَوْلَ الْحِمَى يُوشِكُ أَنْ يَرْتَعَ فِيهِ، أَلَا وَإِنَّ لِكُلِّ مَلِكٍ حِمًى، أَلَا وَإِنَّ حِمَى اللهِ مَحَارِمُهُ، أَلَا وَإِنَّ فِي الْجَسَدِ مُضْغَةً، إِذَا صَلَحَتْ صَلَحَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، وَإِذَا فَسَدَتْ فَسَدَ الْجَسَدُ كُلُّهُ، أَلَا وَهِيَ الْقَلْبُ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: -ኑዕማን (መስማቱን ለማረጋገጥ) በሁለት ጣቶቹ ወደ ጆሮዎቹ እየጠቆመ፦
"ሐላል (የተፈቀደ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠብቋል። አሻሚ ጉዳዮች ላይ የወደቀም ሰው ሐራም ላይ ወድቋል። የዚህ ሰው አምሳያ ልክ የተከለከለ ክልል ወሰን ዙሪያ እንደሚጠብቅና እንስሳዎቹም ወሰን አልፈው የሰው እርሻ ሊገቡ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። አዋጅ! ለሁሉም ንጉስ ወሰን (ድንበር) አለው። አዋጅ! የአላህ ወሰን (ድንበር) ደግሞ ክልከላው ነው። አዋጅ! ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች ሁሉም ሰውነት ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ሁሉም ሰውነት ይበላሻል። አዋጅ! እሷም ልብ ናት።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነገሮች ሁሉ የሚያገለግል አጠቃላይ መርህን እያብራሩ ነው። ነገሮች ሁሉ በሸሪዐ መሰረት ወደ ሶስት ክፍሎች ይከፈላሉ: ግልፅ ሐላል ፣ ግልፅ ሐራምና ከፍቁድነትና ክልክልነት አንፃር ብዙ ሰው ብይናቸውን የማያውቃቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮች ናቸው።
በሱ ላይ አሻሚ የሆኑበትን ጉዳዮች የተወ ሰው ሀራም ላይ ከመውደቅ በመራቁ ሳቢያ እምነቱ ሰላም ይሆናል፤ ይህን አሻሚ የሆነ ጉዳይ በመፈፀሙ ሳቢያ እሱ ላይ የሚደርስን የሰዎች ትችት ስለማይኖርም ክብሩ ከትችት ሰላም ይሆናል። አሻሚ ጉዳዮችን ያልራቀ ሰው ግን ወይ ሐራም ላይ በመውደቅ ወይ በሰዎች ክብሩ በመዘለፉ ሳቢያ ነፍሱን (ለችግር) ያጋልጣታል። መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አሻሚ ጉዳዮች የሚፈፅምን ሰው ሁኔታ ለማብራራት ምሳሌ ጠቀሱ። እሱም ልክ ባለቤቱ በከለላት ስፍራ አስጠግቶ ከብቶቹን እንደሚያሰማራ እረኛ ነው። ቀስ በቀስ የእረኛው ከብቶች ወደተከለለው ስፍራ ቅርብ ስለሆኑ ክልሉ ውስጥ ዘልቀው ሊበሉ ይቀርባሉ። ልክ እንደዚሁ አሻሚ የሆኑ ጉዳዮችን የሚሰራ ሰው በዚህ መዳፈሩ ሳቢያ ወደ ሐራም ይቃረባል። ቀስበቀስ ሐራም ውስጥ ሊወድቅም ይቀርባል። ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ እንዳለች ገለፁ። (እሷም ልብ ናት።) በሷ መስተካከል ሰውነት ይስተካከላል በሷ መበላሸትም ሰውነት ይበላሻል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ብይናቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮችን መተው መበረታታቱ።