عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«الرَّضَاعَةُ تُحَرِّمُ مَا تُحَرِّمُ الوِلَادَةُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [الأربعون النووية: 44]
المزيــد ...
ከዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ውልደት ክልክል የሚያደርገውን ጥቢ ክልክል ታደርጋለች።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 44]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ውልደት እንደ ኻል (በእናት በኩል ያለ አጎት) ወይም ዐም (በአባት በኩል ያለ አጎት) ወይም ወንድም ወዘተ ክልክል እንደሚያደርገው ሁሉ ጥቢም የሚከለክል መሆኑን ገለፁ። ውልደት ሐላል የሚያደርገውን ህግጋትንም ጥቢም ሐላል ያደርገዋል።