+ -

عَنْ حَكِيمِ بْنِ حِزَامٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، قَالَ:
قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَرَأَيْتَ أَشْيَاءَ كُنْتُ أَتَحَنَّثُ بِهَا فِي الجَاهِلِيَّةِ مِنْ صَدَقَةٍ أَوْ عَتَاقَةٍ، وَصِلَةِ رَحِمٍ، فَهَلْ فِيهَا مِنْ أَجْرٍ؟ فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَسْلَمْتَ عَلَى مَا سَلَفَ مِنْ خَيْرٍ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1436]
المزيــد ...

ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ ዘመን በምፅዋት፣ ነፃ በማውጣትና ዝምድና በመቀጠል የምፈፅማቸው አምልኮዎች ነበሩ በእነሱ እመነዳለውን?" አልኳቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለው መለሱለት፦ "ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1436]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ካፊር የሰለመ ጊዜ ከመስለሙ በፊት በጃሂሊያ ዘመን ይሠራቸው በነበሩት እንደ ሰደቃ፣ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ዝምድና መቀጠል የመሰሉ መልካም ሥራዎች እንደሚመነዳ አብራሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ካፊር በዱንያ ለሠራቸው መልካም ሥራዎች በዛው ክህደት ላይ ከሞተ በአኺራ አይመነዳበትም።
ተጨማሪ