عَنْ أَبِي مُوسَى رَضيَ اللهُ عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَثَلُ مَا بَعَثَنِي اللَّهُ بِهِ مِنَ الهُدَى وَالعِلْمِ كَمَثَلِ الغَيْثِ الكَثِيرِ أَصَابَ أَرْضًا، فَكَانَ مِنْهَا نَقِيَّةٌ، قَبِلَتِ المَاءَ، فَأَنْبَتَتِ الكَلَأَ وَالعُشْبَ الكَثِيرَ، وَكَانَتْ مِنْهَا أَجَادِبُ، أَمْسَكَتِ المَاءَ، فَنَفَعَ اللَّهُ بِهَا النَّاسَ، فَشَرِبُوا وَسَقَوْا وَزَرَعُوا، وَأَصَابَتْ مِنْهَا طَائِفَةً أُخْرَى، إِنَّمَا هِيَ قِيعَانٌ لاَ تُمْسِكُ مَاءً وَلاَ تُنْبِتُ كَلَأً، فَذَلِكَ مَثَلُ مَنْ فَقُهَ فِي دِينِ اللَّهِ وَنَفَعَهُ مَا بَعَثَنِي اللَّهُ بِهِ، فَعَلِمَ وَعَلَّمَ، وَمَثَلُ مَنْ لَمْ يَرْفَعْ بِذَلِكَ رَأْسًا، وَلَمْ يَقْبَلْ هُدَى اللَّهِ الَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 79]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"አላህ በርሱ የላከኝ ቅናቻና እውቀት ምሳሌው መሬት ላይ እንደወረደ ብዙ ዝናብ ምሳሌ ነው። ዝናቡ ካገኘው መሬት መካከል ውሃውን የመጠጠች፣ በዛውም ደረቅ ሳርና በርካታ እርጥብ ሳሮችን ያበቀለች ለምለም መሬት አለች፤ የዘነበውን ውሃ የምታቁርና አላህ በርሷ ሰዎችን የሚጠቅምበት ከርሷም የሚጠጡባት፣ ከብቶቻቸውንና ዘራቸውንም የሚያጠጡበት ደረቅ መሬትም አለች፤ ይህቺ ዝናብ ሌላም የመሬትን ክፍል አግኝታለች። ይህም የመሬት ክፍል ወይ ውሃን አያቁር ወይ ሳር አያበቅል የሆነ ለጥ ያለ ደረቅ መሬት ነው። ይህም ምሳሌ አላህ እኔን የላከበት የሆነውን የአላህን ሃይማኖት ተገንዝቦ አላህ በዲኑ ተጠቃሚ ያደረገው፤ ተምሮም ያስተማረ ሰው ምሳሌ እና ለዚህ አላህ እኔን የላከበት ለሆነው ሃይማኖት ራሱንም ቀና ያላደረገ የአላህንም ቅን መመርያ ያልተቀበለ ሰው ምሳሌ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 79]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላማ ላይ የሚያደርስ የሆነውን እርሳቸው ይዘውት በመጡት መንገድና መመሪያ እንዲሁም ሸሪዓዊ እውቀት የሚጠቀምን ሰው ሁኔታው አስገርሟቸው ብዙ ዝናብ በሚዘንብበት ምድር ምሳሌ አደረጉት። ይህ የምድር ክፍልም ሶስት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያውም: የዝናብን ውሃ የምትቀበልና ደረቁንም ይሁን እርጥቡን ቡቃያ የምታበቅል ሰዎችም በርሷ የሚጠቀሙባት ምርጥና ለምለም መሬት ናት። ሁለተኛዋም: መሬቷ አዝርዕት ባታበቅልም ቢያንስ ውሃን የምታቁር ናት። ይህቺም መሬት ሰዎች እንዲጠቀሙባት ውሃን ትይዛለች። ሰዎችም ይጠጡባታል፣ እንስሶቻቸውንና አዝርዕታቸውንም ያጠጡባታል። ሶስተኛው: ቀጥ ያለች እና ለስላሳ መሬት ናት። ውሃንም አትይዝም። አዝርዕትንም አታበቅልም። ይህቺም መሬት ለራሷም በዚህ ውሃ አልተጠቀመች፤ ሰዎችም በርሷ አልተጠቀሙም። ልክ እንደዚሁ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተላኩበትን እውቀትና መመሪያ የሚሰሙ ሰዎች ሶስት ክፍሎች አላቸው። የመጀመሪያው: የአላህን ሃይማኖት ያወቀና የተገነዘበ፣ በእውቀቱ የሚሰራና ሌላውንም የሚያስተምር ነው። ይህም ልክ እንደምርጥ መሬት ምሳሌ ነው። ለራሷም ዝናቡን ጠጥታ ተጠቅማለች። ቡቃያን አብቅላም ሌላውን ጠቅማለች። ሁለተኛው: እውቀትን ሸምድዷል ነገር ግን ከሚያውቀው እውቀት ግንዛቤና አስተምህሮቶችን ማውጣጣት አይችልም። እውቀትን ሰብስቧል። በዘመኑ የሚያስፈልግን እውቀትን አጠቃሎ አውቋል። ነገር ግን እውቀቱ ፍሬያማ አይደለም ወይም ሰብስቦ የሸመደደውን አልተረዳውም። እርሱ ለሌሎች መሳሪያ ነው የሆነው። የዚህም ምሳሌ ውሃ የሚጠራቀምበትና ሰዎችም በውሃው እንደሚጠቀሙበት መሬት ምሳሌ ነው። ሶስተኛው: እውቀትን እየሰማ የማይሸመድድ፣ በርሱም የማይተገብርና ለሌላውም የማያስተላልፍ ሰው ነው። የዚህም ሰው ምሳሌ ቡቃያም የማያበቅል፣ ውሃንም የማያቁርና የማይቀበል ወይም ሌላው እንዳይጠቀመው ውሃውን የሚያበላሽ የሆነ እንደለስላሳ መሬት ምሳሌ ነው።