عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمُشُونَ بها وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ، فَقُلْتُ: مَنْ هَؤُلَاءِ يَا جِبْرِيلُ، قَالَ: هَؤُلَاءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ، وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ».
[حسن] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 4878]
المزيــد ...
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
«ወደ ሰማይ እንዳርግ በተደረግኩበት ወቅት የነሃስ ጥፍር ባላቸውና በነዛም ጥፍሮች ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን በሚቧጭሩ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም "ጂብሪል ሆይ! እነዚህ እነማን ናቸው?" ብዬ ጠየቅኩት። እርሱም "እነዚህ የሰዎችን ስጋ የሚበሉና የሰዎችን ክብር የሚያጎድፉ ናቸው።" በማለት መለሰልኝ።»
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4878]
ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - በኢስራእና ሚዕራጅ ምሽት ወደ ሰማይ በወጡበት ወቅት የነሃስ ጥፍሮች ባሏቸውና ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውንም በሚቧጭሩና በሚቦጭቁ ሰዎች በኩል እንዳለፉ ተናገሩ። ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎች በዚህ ቅጣት እንዲመነዱ ያደረጋቸው ምንድነው? ብለው ጠየቁት። ጂብሪልም ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎችን የሚያሙና ያለአግባብ ስለሰዎች ክብር የሚናገሩ ናቸው። ብሎ መለሰላቸው።