+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه:
أَنَّ رَجُلًا قَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ إِنَّ لِي قَرَابَةً أَصِلُهُمْ وَيَقْطَعُونِي، وَأُحْسِنُ إِلَيْهِمْ وَيُسِيئُونَ إِلَيَّ، وَأَحْلُمُ عَنْهُمْ وَيَجْهَلُونَ عَلَيَّ، فَقَالَ: «لَئِنْ كُنْتَ كَمَا قُلْتَ، فَكَأَنَّمَا تُسِفُّهُمُ الْمَلَّ وَلَا يَزَالُ مَعَكَ مِنَ اللهِ ظَهِيرٌ عَلَيْهِمْ مَا دُمْتَ عَلَى ذَلِكَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2558]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:
«አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ቅርብ ዘመዶች አሉኝ። ዝምድናቸውን እቀጥላለሁ፤ እነርሱ ይቆርጡኛል። እኔ መልካም እውልላቸዋለሁ፤ እነርሱ መጥፎ ያደርጉብኛል። እኔ እታገሳቸዋለሁ፤ እነርሱ ግን ፀያፍ ተግባር ይፈፅሙብኛል።" እርሳቸውም "እንዳልከው ከሆነ አንተ ትኩስ አመድ እያቃምካቸው ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ እስከዘወተርክ ድረስም ከአላህ የሆነ አጋዥ ከአንተ ጋር አይወገድም።" አሉት።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2558]

ትንታኔ

አንድ ሰውዬ ቅርብ ዘመዶች እንዳሉትና ከነርሱም ጋር በመልካም መስተጋብር እንደሚኗኗር እነርሱ ግን ከዚህ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እንደሚኗኗሩት ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስሞታ አቀረበ። እርሱ ይቀጥላቸዋልም፤ ይጠይቃቸዋልም፤ እነርሱ ግን ይቆርጡታል። በበጎነትና በታማኝነት ለነርሱ መልካም ቢውልም እነርሱ ግን በግፍና በድርቅና መጥፎ ይሰሩበታል። ይታገሳቸዋልም፤ ይቅር ይላቸዋልም፤ እነርሱ ግን በፀያፍ ንግግርና ተግባር ይቅርታውን ችላ ይላሉ። ከነዚህ ከተጠቀሱት ተግባራቸው ጋር ዝምድና መቀጠሌን ልግፋበትን?
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ አሉት: እንዳወሳኸው ከሆነ አንተ ራሳቸውን እንዲያዋርዱና እንዲንቁ ነው ያደረግካቸው። በጎ መዋልህ በዝቶላቸው የነርሱ ነፍስ ግን ፀያፍ ተግባር ብቻ መስራቱ ልክ ትኩስ አመድ እንዳበላሀቸው ነው። አንተ ባወሳህልኝ በጎ መዋል ላይ እስከዘወተርክና እነርሱም ላንተ መጥፎ ማድረግ ላይ እስከዘወተሩ ድረስ በነርሱ ላይ የሚያግዝህና የነርሱን ማወክ የሚከላከልልህ ከአላህ ዘንድ የሆነ አጋዥም ከአንተ አይወገድም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መጥፎ ስራን በጥሩ መመለስ መጥፎ አድራጊውን ወደ ትክክል ይመልሳል ተብሎ ይታሰባል። አላህ እንዲህ እንዳለው: {በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ (መጥፎይቱን) ገፍትር። ያን ጊዜ ያ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይሆናል።}
  2. ጉዳት እየደረሰበት ራሱ የአላህን ትእዛዝ መስራቱ አማኙ ባሪያ የአላህን እገዛ እንዲያገኝ ምክንያት ይሆነዋል።
  3. ዝምድና መቁረጥ በዱንያ ቅጣትና ህመም በመጪው አለም ደግሞ ወንጀልና ሒሳብ ይጠብቀዋል።
  4. አንድ ሙስሊም በመልካም ስራው ምንዳውን ማሰብ ይገባዋል። መልካም ስራውን ከመስራትም የሰዎች ማወክና ማደናቀፍ ከመልካም ልማዱ አያቋርጠውም።
  5. ዝምድናን ከቀጠሉት ጋር ውለታን የሚመልስ ዝምድና ቀጣይ አይባልም። ነገር ግን ትክክለኛ ዝምድና ቀጣይ የሚባለው ዝምድናው የተቆረጠች ጊዜ የሚቀጥላት ነው።