عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعت النبي صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَنْ حَجَّ لِلهِ فَلَمْ يَرْفُثْ وَلَمْ يَفْسُقْ رَجَعَ كَيَوْمِ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1521]
المزيــد ...
ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ብሏል፦
"ሚስቱን ሳይገናኝ እንዲሁም ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችበት ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1521]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሚስቱን ሳይገናኝ - "ረፈሥ" የሚለው ቃል ፆታዊ ግንኙነትንም ይሁን መሳሳምና መተሻሸትን የመሰሉ የግንኙነት መንደርደሪያዎችን እንዲሁም ፀያፍ የቃል አጠቃቀምንም የሚያጠቃልል ቃል ነው። ወንጀልና ኃጢዓት በመፈፀም - ሳያምፅ ‐ ሐጅን ያከናወነ ያለውን ደረጃ ገለፁ። አመጽ ውስጥ ከሚካተቱት መካከል በኢሕራም ጊዜ የተከለከለን ማድረግ ይገኝበታል። በዚህ መልኩ ሐጅን ያከናወነ ሰው ልክ ህፃን ልጅ ከወንጀል የፀዳ ሆኖ እንደሚወለደው እርሱም ከወንጀሉ የተማረ ሆኖ ከሐጅ ይመለሳል።