+ -

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ:
قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِامْرَأَةٍ مِنَ الْأَنْصَارِ سَمَّاهَا ابْنُ عَبَّاسٍ فَنَسِيتُ اسْمَهَا: «مَا مَنَعَكِ أَنْ تَحُجِّي مَعَنَا؟» قَالَتْ: لَمْ يَكُنْ لَنَا إِلَّا نَاضِحَانِ فَحَجَّ أَبُو وَلَدِهَا وَابْنُهَا عَلَى نَاضِحٍ وَتَرَكَ لَنَا نَاضِحًا نَنْضِحُ عَلَيْهِ، قَالَ: «فَإِذَا جَاءَ رَمَضَانُ فَاعْتَمِرِي، فَإِنَّ عُمْرَةً فِيهِ تَعْدِلُ حَجَّةً».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1256]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢብኑ ዐባስ በስሟ ጠርቶ ለነገረኝ እኔ ግን ስሟን ለራሳኋት አንዲት የአንሷር ሴት እንዲህ አሏት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" እርሷም "እኛ ከሁለት ግመል በቀር ሌላ አልነበረንም። የልጇ አባትና ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ አደረጉበት፤ ውሃ የምናመላልስበትን አንድ ግመል ደግሞ ለኛ ተወልን።" አለች። እርሳቸውም "ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1256]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሰናበቻ ሐጅ የተመለሱ ጊዜ ሐጅ ላላደረገች ከአንሷር ለሆነች ሴት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" አሏት።
ሁለት ግመል እንደነበራቸው፤ ባሏና ወንድ ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ እንዳደረጉና ሌላኛውን ደግሞ ከጉድጓድ ውሃ እንዲያመላልሱበት እንደተወላቸው በመንገር ያልሄደችበትን ምክንያቷን ገለፀችላቸው።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዑምራን በረመዳን ወር በመፈፀም የሚገኘው ምንዳ የሐጅን ምንዳ የሚስተካከል እንደሆነ ነገሯት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በረመዳን ወር ዑምራ ማድረግ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
  2. በረመዳን ውስጥ ዑምራ ማድረግ ሐጅ ከማድረግ ጋር በምንዳው ይስተካከላል እንጂ ግዴታ የሆነበትን ሐጅ ያስቀርለታል ማለት አይደለም።
  3. የወቅቶች ትሩፋት (ክብር) መጨመር የሥራዎችንም ምንዳ እንዲጨምር ያደርጋል። ከዚህም ውስጥ በረመዳን የሚሠራ ሥራ አንዱ ነው።