+ -

عن عبد الله بن عُمر وأبي هريرة رضي الله عنهما أنهما سمعا رسول الله صلى الله عليه وسلم، يقول على أعواد منبره:
«لَيَنْتَهِيَنَّ أَقْوَامٌ عَنْ وَدْعِهِمُ الْجُمُعَاتِ أَوْ لَيَخْتِمَنَّ اللهُ عَلَى قُلُوبِهِمْ، ثُمَّ لَيَكُونُنَّ مِنَ الْغَافِلِينَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 865]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመርና አቡ ሁረይራ ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እነርሱ የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሚንበራቸው እንጨት ላይ ሆነው እንዲህ ሲሉ ሰሙ:
"ሰዎች ጁመዓዎችን ከመተው ይከልከሉ! አለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 865]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሚንበራቸው ላይ ሆነው ጁመዓን ያለምንም ተቀባይ ምክንያት በስንፍናና በማቃለል ከመተውና ከርሱ ወደኃላ ማለትን አስጠነቀቁ። ያለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ እንደሚያሽግና እንደሚሸፍን፤ በቀልባቸው ላይ እውነትን ከመከተል የሚያቅብ ግርዶሽ እንደሚያደርግና ከዚያም ከመልካም መንገዶች ከሚዘናጉትና ነፍሳቸውም ከአምልኮ ቸልተኛ ከሆኑት እንደምትሆን ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከጁመዓ ሶላት በመቅረት ጉዳይ ጠንካራ ዛቻ መምጣቱንና ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የጁሙዓ ሶላት የነፍስ ወከፍ ግዴታ መሆኑን ያስረዳናል።"
  3. ለኹጥባ ሚንበርን ማዘጋጀት የተደነገገ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
  4. ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "የሐዲሡ ሀሳብ ከሁለት አንዱ የግድ የሚከሰቱ ናቸው ማለት ነው። ወይ ጁመዓዎችን ከመተው መቆጠብ ወይም አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ጁመዓ መተውን መልመድ ቀልብ እንድትሸፈን ይገፋታል። ነፍስንም ከአምልኮ ቸልተኛ ያደርጋታል።"
  5. መካሪና ገሳጭ የሆነ ሰው ሊመክራቸው ያሰባቸውን ግለሰቦች ደበቅ ሊያደርግም ይገባል። ይህም ምክሩ ተቀባይነት እንዲያገኝና ትእዛዙ ተፈፃሚ እንዲሆን የሚያደርግ ስለሆነ ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ