+ -

عَنْ أَبِي الْجَعْدِ الضَّمْرِيِّ رَضيَ اللهُ عنهُ، وَكَانَتْ لَهُ صُحْبَةٌ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ تَرَكَ ثَلَاثَ جُمَعٍ تَهَاوُنًا بِهَا طَبَعَ اللَّهُ عَلَى قَلْبِهِ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 1052]
المزيــد ...

ከአቢ ጀዕድ አድዶምሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - (ከነቢዩ ሶሓቦች መካከልም አንዱ ነበር) እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ሶስት ጁመዓዎችን በመሳነፍ የተወ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።"

[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 1052]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የጁሙዓን ሶላት ከመተው አስጠነቀቁ። ሶስት ጊዜ የጁመዓን ሶላቶች ያለምንም በቂ ምክንያት በመሳነፍና በመዘናጋት የተወ ሰው አላህ መልካም ነገር ወደርሱ እንዳይደርስ በመከልከል ቀልቡን ያሽገዋልም ከመልካም ነገር ይጋርደዋልም።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ኢብኑል ሙንዚር የጁሙዓ ሶላት የነፍስ ወከፍ ግዴታ በመሆኑ ላይ የዑለሞች ስምምነት እንዳለ አውስተዋል።
  2. የጁመዓን ሶላት በስንፍና በተወ ሰው ላይ አላህ ልቡን እንደሚያሽግ ዛቻ መምጣቱን እንረዳለን።
  3. ጁሙዓን በቂ ምክንያት ኖሮት የተወ ሰው ይህ ዛቻ ውስጥ አይካተትም።
  4. ሸውካኒይ እንዲህ ብለዋል: "(ሶስት ጁሙዓዎች) ማለታቸው ጁሙዓዎቹ ተከታትለውም ሆነ ተበታትነው በጥቅሉ ከተተዉ በየዓመቱ አንድ አንድ ጁመዓ ቢተው እንኳ ከሶስተኛዋ በኋላ አላህ ቀልቡን ያሽጋል ማለት ሊሆንም ይችላል። የሒዲሡ ግልፅ መልዕክትም ይኸው ነው። ሶስት ተከታታይ ጁሙዓዎች ማለት ተፈልጎበት ሊሆንም ይችላል።"
ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ