عَنْ أُمِّ سَلَمَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها أَنَّهَا قَالَتْ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ:
«مَا مِنْ مُسْلِمٍ تُصِيبُهُ مُصِيبَةٌ فَيَقُولُ مَا أَمَرَهُ اللهُ: {إِنَّا لِلهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ} [البقرة: 156]، اللَّهُمَّ أْجُرْنِي فِي مُصِيبَتِي، وَأَخْلِفْ لِي خَيْرًا مِنْهَا، إِلَّا أَخْلَفَ اللهُ لَهُ خَيْرًا مِنْهَا»، قَالَتْ: فَلَمَّا مَاتَ أَبُو سَلَمَةَ قُلْتُ: أَيُّ الْمُسْلِمِينَ خَيْرٌ مِنْ أَبِي سَلَمَةَ؟ أَوَّلُ بَيْتٍ هَاجَرَ إِلَى رَسُولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم، ثُمَّ إِنِّي قُلْتُهَا، فَأَخْلَفَ اللهُ لِي رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 918]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ከኡሙ ሰለማ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"አንድም መከራ አጋጥሞት አላህ እንዳዘዘው ‹{ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] አልላሁመእጁርኒ ፊ ሙሲበቲ፣ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ› የሚል ሙስሊም የለም አላህ ከዛ የተሻለ ነገር ቢተካለት እንጂ።"» ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: "አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለና?! ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ይህንን ዱዓ አልኩኝ። አላህም ለኔ የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።" ትርጉሙም ({እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} [አልበቀራ:156] አላህ ሆይ በመከራዬ ምንዳን ስጠኝ። ከደረሰበኝ መከራ የተሻለንም ተካልኝ።) ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 918]
የአማኞች እናት ኡሙ ሰለማ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - አንድ ጊዜ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ እንደሰማች አወሳች: አንድም መከራ የሚደርስበትና አላህ ለርሱ የመረጠለትን ይህንን ውዳሴ የሚል ሙስሊም የለም: {ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን} [አልበቀራ:156] ትርጉሙም {እኛ ለአላህ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን።} (አላሁመእጁርኒ) አላህ ሆይ! በደረሰበኝ መከራ የትእግስቴን ምንዳ ስጠኝ! (ፊ ሙሲበቲ) (ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሃ) ከርሱ የተሻለንም ለኔ ተካልኝ አይልም አላህ ለርሱ ከደረሰበት መከራ የተሻለን ቢለውጥለት እንጂ። ኡሙ ሰለማ እንዲህ አለች: አቡ ሰለማ የሞተ ጊዜ እንዲህ አልኩኝ: "ከአቡ ሰለማ የተሻለ ሙስሊም ከቶ ማን አለ? ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በቅድሚያ የተሰደደ ቤተሰብ ነው። ከዚያም ግን አላህ አግዞኝ ይህንን ውዳሴ ተናገርኩት። አላህም ለኔ ከአቡ ሰለማ የተሻሉትን የአላህን መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተካልኝ።"