عَنْ يحيى بنِ عُمَارةَ المَازِنِيِّ قَالَ:
شَهِدْتُ عَمْرَو بْنَ أَبِي حَسَنٍ سَأَلَ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ زَيْدٍ، عَنْ وُضُوءِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَدَعَا بِتَوْرٍ مِنْ مَاءٍ، فَتَوَضَّأَ لَهُمْ وُضُوءَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَأَكْفَأَ عَلَى يَدِهِ مِنَ التَّوْرِ، فَغَسَلَ يَدَيْهِ ثَلاَثًا، ثُمَّ أَدْخَلَ يَدَهُ فِي التَّوْرِ، فَمَضْمَضَ وَاسْتَنْشَقَ وَاسْتَنْثَرَ، ثَلاَثَ غَرَفَاتٍ، ثُمَّ أَدْخَلَ يَدَهُ فَغَسَلَ وَجْهَهُ ثَلاَثًا، ثُمَّ غَسَلَ يَدَيْهِ مَرَّتَيْنِ إِلَى المِرْفَقَيْنِ، ثُمَّ أَدْخَلَ يَدَهُ فَمَسَحَ رَأْسَهُ، فَأَقْبَلَ بِهِمَا وَأَدْبَرَ مَرَّةً وَاحِدَةً، ثُمَّ غَسَلَ رِجْلَيْهِ إِلَى الكَعْبَيْنِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 186]
المزيــد ...
ከየሕያ ቢን ዑማረህ አልማዚኒይ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ዐምር ቢን አቢ ሐሰን ለዐብደላህ ቢን ዘይድ ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዉዱእ አደራረግ ሲጠይቁ ተገኝቼ ነበር። ውሃ የያዘ እቃ እንዲመጣላቸው ጠየቁ። የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው። ከዉዱእ እቃው ውሃን ወደ እጃቸው በማፍሰስ ሶስት ጊዜ እጃቸውን አጠቡ። ቀጥሎ እጃቸውን ወደ እቃው በመክተት ሶስት ጊዜ ውሃ እየዘገኑ ተጉመጠመጡ፤ አፍንጫቸው ውስጥ ውሃ በመክተትም አወጡ። ቀጥሎ እጃቸውን በመክተት ሶስት ጊዜ ፊታቸውን ታጠቡ። ቀጥሎ ሁለት ጊዜ ሁለት እጃቸውን እስከ ክርኖቻቸው አጠቡ። ቀጥሎ እጃቸውን በመክተት ጭንቅላታቸውን አበሱ። እጃቸውን አንድ ጊዜ ወደኋላ ወስደው ወደፊት መለሷቸው። ቀጥሎ ሁለት እግሮቻቸውን እስከ ቁርጭምጭሚታቸው ድረስ አጠቡ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 186]
ዐብደላህ ቢን ዘይድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ በተግባራዊ መልኩ ገለፁ። አነስ ያለ ውሃ የያዘ እቃ እንዲያመጣላቸው ጠየቁ። በመጀመሪያ ሁለት መዳፋቸውን በማጠብ ጀመሩ። እቃውን ዘንበል በማድረግ ውሃውን እያፈሰሱ ሁለት እጆቻቸውን ከእቃው ውጪ አድርገው ሶስት ጊዜ አጠቧቸው። ቀጥለውም እጃቸውን እቃ ውስጥ በመክተት ከርሱ ሶስት ጊዜ እየዘገኑ በያንዳንዱ መዝገን ተጉመጠመጡ አፍንጫቸውም ውስጥ ውሃ እየከተቱ አስወጡ። ቀጥሎ ከእቃው በመዝገን ሶስት ጊዜ ፊታቸውን አጠቡ። ቀጥሎ ከእቃው በመዝገን ሁለት እጃቸውን እስከ ክርናቸው ድረስ ሁለት ጊዜ አጠቡ። ቀጥሎ ሁለት እጃቸውን እቃ ውስጥ በመክተት ካረጠቡ በኋላ ጭንቅላታቸውን በሁለት እጆቻቸው አበሱ። ከጭንቅላታቸው ፊትለፊት በመጀመር ወደ ማጅራታቸው እስኪደርስ ድረስ አበሱ። ቀጥሎ ወደ ጀመሩበት ስፍራ እስኪደርስ ድረስ ሁለት እጃቸውን መለሷቸው። ቀጥሎ ሁለት እግሮቻቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው ጋር አጠቡ።