عن عائشةَ أمِّ المؤْمنِين رضي الله عنها قالت:
لَمْ يَكُنِ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى شَيْءٍ مِنَ النَّوَافِلِ أَشَدَّ مِنْهُ تَعَاهُدًا عَلَى رَكْعَتَيِ الفَجْرِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1169]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1169]
የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንዲህ ብላ ተናገረች: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) እጅግ ተጠባብቀውና ዘውትረው እንደሚሰግዱት ያህል ምንም ሱና ሶላት ተጠባብቀውና ዘውትረው አይሰግዱም ነበር።