عَنْ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
أَنَّهُ جَاءَ إِلَى الحَجَرِ الأَسْوَدِ فَقَبَّلَهُ، فَقَالَ: إِنِّي أَعْلَمُ أَنَّكَ حَجَرٌ، لاَ تَضُرُّ وَلاَ تَنْفَعُ، وَلَوْلاَ أَنِّي رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُقَبِّلُكَ مَا قَبَّلْتُكَ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1597]
المزيــد ...
ከዑመር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - እንደተላለፈው:
"ዑመር ወደ ጥቁሩ ድንጋይ (ሐጀሩል አስወድ) መጣና ሳመው። እንዲህም አለ: እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1597]
የአማኞች መሪ ዑመር ቢን ኸጧብ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - በካዕባ ማእዘን ወደሚገኘው ጥቁር ድንጋይ መጣና ሳመው። እንዲህም አለ "እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"