عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ مَسعودٍ رضي الله عنه عن رَسولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم قال:
«الطِّيَرَةُ شِرْكٌ، الطِّيَرَةُ شِرْكٌ، الطِّيَرَةُ شِرْكٌ، -ثلاثًا-»، وَمَا مِنَّا إِلَّا، وَلَكِنَّ اللهَ عَزَّ وَجَلَّ يُذْهِبُهُ بِالتَّوَكُّلِ.

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። (አሉ ሶስት ጊዜ)' ከኛ መካከል በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት እንጂ አንድም የለም። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ በመመካታችን ምክንያት ያስወግደዋል።"

Sahih/Authentic. - [Ibn Maajah]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከገድ እምነት አስጠነቀቁ። እርሱም: በሚሰማም ይሁን በሚታይ ነገር፤ በበራሪም ሆነ በእንስሳም ሆነ በህመምተኞች (አካል ጉዳተኞች)፤ በቁጥሮችም ሆነ በቀናት ወይም ከነዚህ ውጪ ባሉ ማንኛውም ነገርም ቢሆን ገደ ቢስነትን ማመን ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በራሪን የጠቀሱት ጃሂሊዮች ዘንድ የታወቀ ስለሆነ ነው። የዚህ ስራ መሰረቱም ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያሉ ስራዎችን ለመጀመር ሲሉ በራሪን ይለቁና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ከበረረ ገድ አለኝ ብሎ ወደ ፈለገበት ጉዳይ ይሄዳል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረ ደግሞ ገደ ቢስ ነኝ ብሎ ያሰበውን ጉዳይ ከመፈፀም ይቆጠባል። ይህ ነገር ሺርክ መሆኑንም ተናገሩ። ገደቢስነትን ማመን ሺርክ የሆነውም መልካምን ከአላህ በቀር የሚያመጣ ስለሌለና፤ መጥፎንም ብቸኛና አጋር ከሌለው አላህ በቀር የሚከላከል ስለሌለ ነው።
ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሙስሊም ቀልብ ውስጥ አንዳች ገደቢስ እምነት ሊከሰት እንደሚችል፤ ነገር ግን ሰበቡን ከማድረስ ጋር በአላህ ላይ በመመካት ማስወገድ እንዳለበት ገለፁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የገድ እምነት ውስጥ ከአላህ ውጪ በሆነ አካል ላይ ልብን ማንጠልጠል ስላለ ሺርክ ነው።
  2. አንገብጋቢ ጉዳዮች ልብ ውስጥ እንዲሸመደዱና እንዲፀኑ ሲባል መደጋገም ወሳኝ እንደሆነ እንረዳለን።
  3. የገድ እምነትን በአላህ ላይ መመካት ያስወግደዋል።
  4. ብቸኛ በሆነው አላህ ላይ መመካት መታዘዙንና ልብም በርሱ ላይ መንጠልጠል እንዳለበት እንረዳለን።