+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا اسْتَيْقَظَ أَحَدُكُمْ مِنْ مَنَامِهِ فَلْيَسْتَنْثِرْ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، فَإِنَّ الشَّيْطَانَ يَبِيتُ عَلَى خَيَاشِيمِهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 238]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 238]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከእንቅልፉ የነቃ ሰው ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ እንዲያወጣ አነሳሱ። ይህም ሸይጧን በአፍንጫ ውስጥ ስለሚያድር ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከእንቅልፉ ለነቃ ሰው ሁሉ ከአፍንጫው የሸይጧንን ፋና ለማስወገድ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ማውጣት እንደተደነገገ እንረዳለን። ዉዹእ የሚያደርግ ከሆነ ደግሞ በዚህ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ በማውጣት መታዘዙ ይበልጥ አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ ይሆናል።
  2. ከአፍንጫ ውሃ ማስወጣቱ አሟልቶ ወደ አፍንጫ ውሃ ከማስገባት የሚመደብ ነው። ወደ አፍንጫ ውስጥ ውሃ ማስገባት የአፍንጫን ውስጥ ማፅዳት ነው። ማስወጣቱ ደግሞ ከውሃው ጋር ቆሻሻውን እንዲወጣ ማድረግ ነውና።
  3. ሐዲሡ ውስጥ "ያድራልና" የሚለው ቃል ይህ ድርጊት በምሽት እንቅልፍ መገደቡን ያስረዳናል። ማደር ከምሽት እንቅልፍ ውጪ አይሆንምና። ይህም የምሽት እንቅልፍ መርዘምና ጥልቅ እንቅልፍ የሚጠረጠርበት ቦታ ስለሆነ ነው።
  4. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሸይጧን የሰው ልጅ በማያውቀው መልኩ ከርሱ ጋር አብሮ እንደሚቆራኝ ይጠቁማል።