+ -

عَن عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قَالَ: سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الْمَاءِ وَمَا يَنُوبُهُ مِنَ الدَّوَابِّ وَالسِّبَاعِ، فَقَالَ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا كَانَ الْمَاءُ قُلَّتَيْنِ لَمْ يَحْمِلِ الْخَبَثَ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 63]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንስሶችና አውሬዎች ተመላልሰው ስለሚጠጡት ውሃ ተጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ:
"ውሃው ሁለት 'ቁለተይን' ከደረሰ ነጃሳን አይሸከምም።"»

[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 63]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንስሳዎችና አውሬዎች ለመጠጣትና ለመሳሰሉት ስለሚመላለሱበት ውሃ ንፁህነት ብይን ተጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ውሃ መጠኑ ሁለት ትላልቅ እንስራዎችን የደረሰ ጊዜ ‐ 210 ሊትር የሚሆን ብዛት ማለት ነው። ‐ ብዙ ውሃ ስለሆነ ከሶስቱ ባህሪያቶቹ አንዱ በነጀሳ እስካልተለወጠ ድረስ እነርሱም ቀለሙ ወይም ጣዕሙ ወይም ሽታው እስካልተለወጠ ድረስ አይነጀስም አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ውሃ ከሶስቱ ባህሪያቶቹ አንዱ በነጃሳ የተለወጠ ጊዜ ማለትም ቀለሙ ወይም ጣዕሙ ወይም ሽታው የተለወጠ ጊዜ ይነጀሳል። ሐዲሡ በአብዛኛው ጊዜ ከሚከሰተው በመንተራስ ነው የተነገረው እንጂ በመገደብ ደረጃ አይደለም።
  2. ውሃ በነጃሳ የተለወጠ ጊዜ ውሃው አነሰም በዛ እንደሚነጀስ ዑለማዎች ባጠቃላይ ተስማምተዋል።