عَن أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ:
سَأَلَ رَجُلٌ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّا نَرْكَبُ البَحْرَ، وَنَحْمِلُ مَعَنَا القَلِيلَ مِنَ الْمَاءِ، فَإِنْ تَوَضَّأْنَا بِهِ عَطِشْنَا، أَفَنَتَوَضَّأُ مِنَ الْبَحْرِ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «هُوَ الطَّهُورُ مَاؤُهُ، الحِلُّ مَيْتَتُهُ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 69]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
«አንድ ሰው የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ በባህር እንሳፈራለን፣ ከኛ ጋርም የተወሰነ ውሃ እንሰንቃለን። በዚህ በያዝነው ውሃ ዉዱእ ብናደርግበት እንጠማለንና በባህር ውሃ ዉዹእ እናድርግን?" የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት መለሱ: "እርሱ ውሃው አፅጂ ነው፤ ውስጡ የሞተም ሐላል ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን ቲርሚዚ - 69]
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "እኛ ለማደን ወይም ለንግድና ለመሳሰሉት በባህር ላይ ጀልባዎችን እንሳፈራለን። ለመጠጥ የሚሆን ትንሽ ውሃንም ከኛ ጋር እንጭናለን። የመጠጡን ውሃ ለዉዹእና ለገላ ትጥበት ከተገለገልን ያልቅብንና የምንጠጣውን አናገኝም። ታዲያ በባህር ውሃ ዉዹእ ማድረግ ለኛ ይፈቀድልናል እንዴ?"
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለባህሩ ውሃ እንዲህ አሉ "ውሃው ንፁህም አፅጂም ነው። በርሱም ዉዹእ ማድረግ፣ ገላ መታጠብ ይፈቀዳል። ከርሱ የሚወጡን አሳዎችንና ሌሎች የባህር እንስሳዎችንም ሙተው ሳይታደኑ ከላይ ተንጣለው ቢገኙ ራሱ መብላት ይፈቀዳል።"