عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ فِي الْجَنَّةِ لَسُوقًا، يَأْتُونَهَا كُلَّ جُمُعَةٍ، فَتَهُبُّ رِيحُ الشَّمَالِ فَتَحْثُو فِي وُجُوهِهِمْ وَثِيَابِهِمْ، فَيَزْدَادُونَ حُسْنًا وَجَمَالًا، فَيَرْجِعُونَ إِلَى أَهْلِيهِمْ وَقَدِ ازْدَادُوا حُسْنًا وَجَمَالًا، فَيَقُولُ لَهُمْ أَهْلُوهُمْ: وَاللهِ لَقَدِ ازْدَدْتُمْ بَعْدَنَا حُسْنًا وَجَمَالًا، فَيَقُولُونَ: وَأَنْتُمْ وَاللهِ لَقَدِ ازْدَدْتُمْ بَعْدَنَا حُسْنًا وَجَمَالًا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2833]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
«ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች። በስተሰሜን ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ትገርፋለች። (በዚህም) ውበትና ቁንጅናን ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅናቸው ጨምሮም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶቻቸውም እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! ከኛ ከተለያቹ በኋላ ውበትና ቁንጅናችሁ ጨምሯል።" እነርሱም ለሚስቶቻቸው "በአላህ እንምላለን! እናንተም ከኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2833]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጀነት ውስጥ የጀነት ሰዎች የሚሰባሰቡበትና መሸጥና መግዛት ሳይጠበቅባቸው የፈለጉትን ነገር የሚወስዱበት ቦታ እንዳለ ተናገሩ። ወደዚህም ስፍራ በየሳምንቱ ይመጣሉ። በሰሜን አቅጣጫ ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ታንቀሳቅሳለች። በዚህም ውበትና ቁንጅና ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅና ጨምረውም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶቻቸውም ለነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! ከኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።" እነርሱም ለሚስቶቻቸው እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! እናንተም ከተለያየን በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።"